ክብራችን አንተ ዝርግፍ ጌጣችን ወታችን ነህ ጌታ አባታችን በጨለማ ላይ የምታበራ የንጋት ኮከብ አንተ ነህና ከፍ በል የይሁዳ አንበሳ ሞትን ገዳይ የዳዊት ዘር ነህ አንተ ኤልሻዳይ ሲኦልን ድል ነስተህ ቀንበር ሰባሪ ዘራችን ይሁን ለአንተ ዘማሪ የአንተ በመሆኔ ኮራሁኝ እኔ የእኔ ነህ ሲለኝ ደስ ደስ አለኝ (2x) አዝ፦ አይቻለሁ (ሆ) በምድር ላይ (ሆ) የእኔ ኢየሱስ ብቻ ጥር የበላይ ሁሉም ገደብ ልክ አለው የእኔ ጌታ ብቻ አቻ የሌለው አቻ የሌለው (3x) ኢየሱስ ነው ወደር የሌለው (3x) ኢየሱስ ነው ምድር አልቻለችም አለቃዋን ይዛ መልሳ ተፋችው ፈጣሪዋን ታዛ ዓለምና ሰይጣን ሲዖል ያልቻለው የእኔ ኢየሱስ ብቻ ነው አቻ የሌለው አቻ የሌለው ወደር የሌለው ኢየሱስሴ ብቻ ሞት ያልበገረው አቻ የሌለው ወደር የሌለው (2x) አዝ፦ አይቻለሁ (ሆ) በምድር ላይ (ሆ) የእኔ ኢየሱስ ብቻ ጥር የበላይ ሁሉም ገደብ ልክ አለው የእኔ ጌታ ብቻ አቻ የሌለው አቻ የሌለው (3x) ኢየሱስ ነው ወደር የሌለው (3x) ኢየሱስ ነው እግሩ ለጋ ነሃስ ዐይኖቹ ነበልባል ነው እርሱን ተመልክቶ የሚቆም ሰው ማነው ስንቱ ጀግና ሞቶ መቃብር ሲቀር ኢየሱስ ተነስቷል አርጓል በክብር ንጉሠ ነገሥት ነው ያለ የነበረ ወደፊትም ይኖራል ገና እየከበረ እየተከበረ ገና እየከበረ (2x) ክብራችን አንተ ዝርግፍ ጌጣችን ወታችን ነህ ጌታ አባታችን በጨለማ ላይ የምታበራ የንጋት ኮከብ አንተ ነህና ከፍ በል የይሁዳ አንበሳ ሞትን ገዳይ የዳዊት ዘር ነህ አንተ ኤልሻዳይ ሲኦልን ድል ነስተህ ቀንበር ሰባሪ ዘራችን ይሁን ለአንተ ዘማሪ የአንተ በመሆኔ ኮራሁኝ እኔ የእኔ ነህ ሲለኝ ደስ ደስ አለኝ (2x) አዝ፦ አይቻለሁ (ሆ) በምድር ላይ (ሆ) የእኔ ኢየሱስ ብቻ ጥር የበላይ ሁሉም ገደብ ልክ አለው የእኔ ጌታ ብቻ አቻ የሌለው አቻ የሌለው (3x) ኢየሱስ ነው ወደር የሌለው (3x) ኢየሱስ ነው የዚህ ዓለም ገዢ ሲፎክር ሲያቅራራ ገደልኩት ቀበርኩት እያለ ሲያወራ በትንሳኤው ጉልበት ኢየሱስ ተነሳ ጠላቴም ወደቀ በይሁዳ አንበሳ ሰባቱን ማህተም ቋጠሮን የፈታ ኢየሱስ ብቻ ነው የይሁዳ አንበሳ (3x) የይሁዳ አንበሳ የይሁድ አንበሳ (2x) ለክብሩ (ሆ) ለኃይሉ (ሆ) ቢዘመር (ሆ) ለስሙ (ሆ) ቢወራ በምድር አይበቃም ለእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር (3x) አለኝ ዘምር ለእግዚአብሔር (3x) አለኝ ዘምር ሃሌሉያ እሰይ ኢየሱስ ኢየሱስ አቻ የለውም