Song Lyrics

ለእኔ የምታስበው

Endalkachew Hawaz
Misganawun Aliresawum
አሻግሬ አያለሁ ያንተን መልካምነት ከቶ አልገምትህም አሁን ባለሁበት ታሪክ የምትለውጥ ሁሉንም የምትቀይር እኔ የማመልክህ ድንቅነህ እግዚአብሔር አዝ፦ ለእኔ የምታስበው በጐና ያማረ ነው (3x) አመሰግንሃለሁ (3x) አመሰግንሃለሁ (3x) የተገለጠውን ነገር ጸራለህ በላይ ተሰውረህ ድንቅን ታደርጋለህ ተዐምራትህ ብዙ እጅግ የበዛ ነው ጌታ አሰራርህ ከሁሉም ልዩ ነው አዝ፦ ለእኔ የምታስበው በጐና ያማረ ነው (3x) አመሰግንሃለሁ (3x) አመሰግንሃለሁ (3x) ከሁኔታዎች በላይ ቃልህን አምናለሁ ሚሰማኝን ሳይሆን የሩቁን አያለሁ ከእንግዲህ ታምኜ በእምነት እኖራለሁ የተናገርከኝንም እንዳገኝ አውቃለሁ (2x) ኃይልህ ብዙ ሳለ ጠላቶች ቢዋሹም አንተ ግን አንተ ነህ ከቶ አትለወጥም መልካምነትን በማድረግ ደስ ይለሃልና አቤቱ የእኔ ጌታ ይሁን ለአንተ ምሥጋና አዝ፦ ለእኔ የምታስበው በጐና ያማረ ነው (3x) አመሰግንሃለሁ (3x) አመሰግንሃለሁ (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection