Song Lyrics

ምሥጋናህ ዘወትር በአፌ ነው

Endalkachew Hawaz
Misganawun Aliresawum
አዝ፦ ምሥጋናህ ዘወትር በአፌ ነው (4x) ላመሰግንህ እወዳለሁ (3x) ላመሰግንህ እፈቅዳለሁ (3x) ቀንበረን ከጫንቃዬ ላይ ሰበርከው አሃሃሃ የከበደኝን ሸክሜን አራገፍከው ባዶነቴን በፍቅርህ ሞላኸው ደስታዬን ከወይን ፍሬ ይልቅ አበዛኸው ታዲያ ምን ልክፈልህ ታዲያ ምኔን ልስጥህ እንዲሁ አንተን ልባርክህ (2x) ምሥጋናህ ዘወትር በአፌ ነው (4x) ላመሰግንህ እወዳለሁ (3x) ላመሰግንህ እፈቅዳለሁ (3x) በሕይወት መዝገብህ ላይ ስሜን ጻፍከው ኑሮዬን ታሪኬን በሙሉ ለወጥከው በደስታ ዘይት ራሴን ስትቀባ ሰላምን ኢኸው በቤቴ ውስጥ ገባ ታዲያ ምን ልክፈልህ ታዲያ ምኔን ልስጥህ እንዲሁ አንተን ልባርክህ (2x) ተመስገን ለዘላለም ተመስገን (2x) ተመስገን ለዘላለም ተመስገን (2x) ሊቋቋሙን ከቶ አልቻሉም ጠላቶቼ በስምህ አሸነፍኳቸው ተዋግቼ እግሬን በአንገታቸው ላይ አኑሬያለሁ በደስታ የድል ዝማሬን ዘምራለሁ መክበቡን ዙሪያዬን ከቦኝ ነበረ ያሰብክልኝ ስፍራ እንዳልደርስ ብዙ ጣረ አንተ ግን ሁሉን ጥሰህ አሳለፍከኝ ጠላቴ ዓይኑ እያየ ከፍ አረከኝ ታዲያ ምን ልክፈልህ ታዲያ ምኔን ልስጥህ እንዲሁ አንተን ልባርክህ (2x) ተመስገን ለዘላለም ተመስገን (2x) ተመስገን ለዘላለም ተመስገን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection