የምሥጋናን መስዋዕት እሰዋለሁ የከንፈሬን ፍሬ አቀርባለሁ እግዚአብሔር ብቻህን አምላክ ነህና ልትወደስ ይገባሃልና (2x) ይገባሃል አሜን ይገባሃል (4x) . (1) . በበገና በአዲስ ዝማሬ በምሥጋና እቀኝልሃለሁኝ በክብሬ ዝማሬም ይፈልቃል ከከንፈሬ ክብር ለአንተ ሃሌሉያ ክብር ላንተ (4x) ይገባሃል አሜን ይገባሃል (4x) ያደረጋትን ድንቅ ልጸሙ በአደባባዮቹ የምትቆሙ እስኪ ተቀኙለት ለዚህ ጌታ ከቅዱሳን ጋራ በደስታ ክብር ለአንተ ሃሌሉያ ክብር ላንተ (4x) ይገባሃል አሜን ይገባሃል (4x) ሠማያትን በስንዝር የለካህ (ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን) የምድርን መሰረት ያጸናህ (ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን) ባሕሩንና የብሱን የለየህ (ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን) የብርታትህን ጉልበት ያሳየኸን (ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን) ሃሌሉያ ሆ ሃሌሉያ (4x) ዙፋንህ ከጥንት ከዘለላለም (ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን) የእኛ ጌታ የሚመስለህ የለም (ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን) የሁሉ አዛዥ የሁሉ የበላይ (ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን) እግዚአብሔር ነህ ብቻህን ኤልሻዳይ (ኦ ሃሌሉያ ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን) ሃሌሉያ ሆ ሃሌሉያ (4x) ሃሌሉያ ሆ ሃሌሉያ (4x)