ምሥጋና ሲያንስህ ነው ዝማሬ ሲያንስህ ነው አምልኮ ሲያንስህ ነው ውዳሴ ሲያንስህ ነው ከአደረከው ጋራ ሳወዳድረው ከሰራኸው ጋራ ሳመዛዝነው (2x) ከተደረገልኝ ነገር አንዱም አይገባኝም ነበር (2x) እንዲሁ በፀጋ ወደህ ከአደረከው ጌታ ክበር እንጂ ሌላ ምን እላለሁ (2x) ሠማያዊ ብርሃን በልቤ ውስጤ በርቷል የጌታዬ ማዳን ነፍሴን አግኝቷታል ከዘለዓለም ጥፋት ከፍርድ አምልጫለሁ በትንሳኤው ጉልበት አዲስ ሰው ሆኛለሁ ኢኸው ምሥጋናዬን ለአንተ አበዛለሁ ኢኸው ዝማሬዬን ለአንተ አበዛለሁ (2x) ምሥጋና ሲያንስህ ነው ዝማሬ ሲያንስህ ነው አምልኮ ሲያንስህ ነው ውዳሴ ሲያንስህ ነው ከአደረከው ጋራ ሳወዳድረው ከሰራኸው ጋራ ሳመዛዝነው ከተደረገልኝ ነገር አንዱም አይገባኝም ነበር (2x) እንዲሁ በፀጋ ወደህ ከአደረከው ጌታ ክበር እንጂ ሌላ ምን እላለሁ (2x) ክቡር ኃያል ጌታ የእስራኤል ተዋጊ በአለቀ ሰዓት ላይ የምስደርስ ታዳጊ አዋጅን በአዋጅ በሥልጣንህ ሽረህ በድል አራመድከኝ ታሪኬን ቀይረህ ኢኸው ምሥጋናዬን ለአንተ አበዛለሁ ኢኸው ዝማሬዬን ለአንተ አበዛለሁ (2x) ምሥጋና ሲያንስህ ነው ዝማሬ ሲያንስህ ነው አምልኮ ሲያንስህ ነው ውዳሴ ሲያንስህ ነው ከአደረከው ጋራ ሳወዳድረው ከሰራኸው ጋራ ሳመዛዝነው ከተደረገልኝ ነገር አንዱም አይገባኝም ነበር (2x) እንዲሁ በፀጋ ወደህ ከአደረከው ጌታ ክበር እንጂ ሌላ ምን እላለሁ (2x) ፊትህ እቀርባለሁ በብዙ ምሥጋና ጌታ ለውለታህ ምላሽ የለኝምና የከንፈሬን ፍሬ እንካ ተቀበለው ሕያው መስዕዋቴ ማደሪያህን ይሙላው ኢኸው ምሥጋናዬን ለአንተ አበዛለሁ ኢኸው ዝማሬዬን ለአንተ አበዛለሁ (2x)