Song Lyrics

ሃሌሉያ

Endalkachew Hawaz
Misganawun Aliresawum
በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ እውነት አለ ። እግዚአብሔር አምልኮንና ምሥጋናን ይወዳል ። ግዑዛን ፍጥረታት እንኳን ይህን ተረድተው ቀንና ሌሊት ሳያቋርጡ ያመልኩታል ። የእጆቹ ሥራ የሆንንና ፍቅሩን ያየን እኛማ እንዴት ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች ሌሊት ለሌሊቱ ቀትር ትናገራለች ድምጻቸውን ከቶ ሳያሰሙ ፍጥረት ሁሉ ለአንተ ሲያዜሙ እኔም ልቤ በዚህ ተደነቀ የምሥጋና ዜማ አፈለቀ ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌ ሃሌሉያ (4x) (ሃሌሉያ) ሃሌ ሃሌሉያ (ክብር ለአንተ ኢየሱስ) ሃሌ ሃሌሉያ ሃሌ ሃሌሉያ (2x) (ሃሌሉያ) ዓይኖቼን ወደ ላይ አቀናለሁ እጆቼን ወደ አንተ አነሳለሁ በእውነት በመንፈስ አመልክሃለሁ በእውነት በመንፈስ አመልክሃለሁ (2x) ሠማያት ክብርህን ያሳየሉ እግዚአብሔር አለ እያሉ ይናገራሉ ሰነፍ በልቡ አምላክ የለም ቢልም የዓለም ምስክር እራስህን አልተውክም የማይታየው ባሕሪህ ታይቷል ለዘለዓለም ኃይልህም ተገልጧል ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) ሃሌሉያ ፀሐይም . (1) . ታወጣለች እስከ ምድር ዳርቻም ድረስ ታዞራታለህ ከዋክብርትም በሌ ት የምትመራ የጨረቃን ብርሃን የምታበራ ከአንተ በቀር ጌታ አምላክ ማነው በህዋ ላይ ሙሉ ስልጣን ያለህ ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) ሃሌሉያ ሃሌ ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) ሃሌ ሃሌሉያ (3x) ኢየሱስ አንተ በሠማይና በምድር መካከል ታላቅ አምላክ ነህ ። እንደ አንተ ያለ የለም ። በሠማይም የለም በምድርም የለም ። ታላቅነት ገናናነት ክብር ምሥጋና ባለጠግነት ሁሉ ለሥምህ ይሁን ። አሜን ! ዓይኖቼን ወደ ላይ አቀናለሁ እጆቼን ወደ አንተ አነሳለሁ በእውነት በመንፈስ አመልክሃለሁ በእውነት በመንፈስ አመልክሃለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection