ከጥንት እንደሰማሁት በዓይኖቼም ደግሞ እንዳየሁት አምላክ ከአንተ በቀር የለም መቼም ቢሆን አይገኝም በምድር ሆነ በሠማይ በየብስ ሆነ በባሕር ላይ በሰው ልጆችም መካከል የለም አንተን የሚስተካከል አዝ፦ ከፍ በል ለዘለዓለም ከፍ በል (4x) አምላኬ ነህ አንተ ለዘለዓለም ንጉሤ ነህ አንተ ለዘለዓለም ጌታዬ ነህ አንተ ለዘለዓለም ከአንተ ሌላ ሌላ የማመልከው የለም ከአንተ ሌላ ሌላ የማመልከው የለም (2x) ሰዎች የሚያመልኳቸው ዛሬም የሚከተሏቸው ብዙ አማልክት ቢሆኖሩም አንዳቸውም እውነት አይደሉም ታላቅ ገናና ኃይለኛ (ገናና ኃይለኛ) ታጋሽ መሃሪ ሞሆንህ ከጥንት ከጥንትም ጀምሮ (ጀምሮ) በእውነት እግዚአብሔር አምላክ ነህ አዝ፦ ከፍ በል ለዘለዓለም ከፍ በል (4x) አምላኬ ነህ አንተ ለዘለዓለም ንጉሤ ነህ አንተ ለዘለዓለም ጌታዬ ነህ አንተ ለዘለዓለም ከአንተ ሌላ ሌላ የማመልከው የለም ከአንተ ሌላ ሌላ የማመልከው የለም (2x) በእኔ ላይ ተሹመሃል ፍቅርህ ልቤን ወርሶታል እውነት በርታልኛለች ነፍሴም አምላኳን አውቃለች ውዴ አንተ የእኔ ነህ እኔም የአንተ ሆኛለሁ በቀረልኝ ዘመን ሁሉ ሳደንቅህ ሳከብርህ ኖራለሁ አዝ፦ ከፍ በል ለዘለዓለም ከፍ በል (8x) ጌታ ሆይ እናከብርሃለን ከፍ እናረግሃለን ። አንተ ብቻ ታላቅ ነህና አንተ ብቻ ጌታ ነህና አንተ ብቻ አምላክ ነህና ። ኦ ከፍ አናደርግሃለን ክበር እንልሃለን ስለ አምላክነትህ እንሰግዳለን ስለ ጌትነት እንሰግዳለን ምህረትህን አይተናልና ኢየሱስ ። ኦ ፍቅርህን ቀምሰናልና በሕይወታችን ልንክደው የማንችለው እውነት በርቶልናልና ኢየሱስ ከፍ ካለው በላይ ከፍ እናደርግሃለን ኦ ሃሌሉያ !