ታላቅነትህን አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (2x) አቤቱ ውበትህን አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (2x) ፊትህ እንደ ፀሐይ የሚያበራ ድምጽህ ነጐድጓድ ነው የሚያስፈራ ምህረትህን በወርቅ የታጠቀ እጅግ ያማረ ነው ውበትህ አዝ፦ አቤቱ ውበትህ እያደነቀ አቤቱ ሥራህን እያደነቀ ታላቅነትህን እያደነቀ ልቤ መልካም ነገርን ይኸው አፈለቀ (2x) እንደፈጣን ፀሓፊ አንደበቴን እከፍታለሁ መቼ ያስችለኛል አምላኬ ክብርህን እያየሁ አመሰግንሃለው አሃሃ አመሰግንሃለሁ (አመሰግንሃለው) አመሰግንሃለው ኦሆሆ አመሰግንሃለሁ የቤትህን ስርዓት አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (2x) አቤቱ ጥበብህን አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (2x) የቤትህን ስርዓት አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (2x) አቤቱ ጥበብህን አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (2x) ስለ አንተ ከሰማሁት ዝና ይልቅ በዓይኔ የማየው ሆነብኝ ድንቅ ስለዚህም ነፍሴ ተማረከች የምሥጋናን ዜማ አፈለቀች አዝ፦ አቤቱ ውበትህ (አቤቱ ውበትህ) እያደነቀ (እያደነቀ) አቤቱ ሥራህን (አቤቱ ሥራህን) እያደነቀ (እያደነቀ) ታላቅነትህን (ታላቅነትህን) እያደነቀ (እያደነቀ) ልቤ መልካም ነገርን (ልቤ መልካም ነገርን) ይኸው አፈለቀ (ይኸው አፈለቀ) (2x) እንደፈጣን ፀሓፊ አንደበቴን እከፍታለሁ መቼ ያስችለኛል አምላኬ ክብርህን እያየሁ አመሰግንሃለው አሃሃ አመሰግንሃለሁ (አመሰግንሃለው) አመሰግንሃለው ኦሆሆ አመሰግንሃለሁ የእጆችህን ሥራ አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (2x) አቤቱ ፍጥረታትን አይቼ ነፍስም አልቀረልኝ (2x) ጨረቃና ፀሐይ ከዋክብት በምድር ላይ ያሉ እንስሳት ሁሉ በአንተ ለአንተ ተፈጥረዋል አምላኬ ሆይ ሥራህ ያስደንቃል አዝ፦ አቤቱ ውበትህን እያደነቀ (አቤቱ ሥራህ) አቤቱ ሥራህ እያደነቀ (ታላቅነትህን) ታላቅነትህን እያደነቀ ልቤ መልካም ነገርን ይኸው አፈለቀ (2x) እንደፈጣን ፀሓፊ አንደበቴን እከፍታለሁ መቼ ያስችለኛል አምላኬ ክብርህን እያየሁ አመሰግንሃለው አሃሃ አመሰግንሃለሁ (አመሰግንሃለው) አመሰግንሃለው ኦሆሆ አመሰግንሃለሁ