የልቤ አምላክ ሆይ ደስታዬ ነህ የልቤ አምላክ ሆይ እረፍቴ ነህ ከአንተ ውጪ ምን ምን ሕይወት አለ ከአንተ ውዲያስ ምን ምንስ ክብር አለ (2x) ሁሉን አግኝቼ አንተን ከማጣ ሁሉን ነገር ኖሮኝ ክብርህ ከሚጐድልብኝ (2x) ሁሉን አጥቼ አንተን ብቻ ባገኝ ይሄ ትርፌ ነው ለእኔ ክብሬ ይህ ነው ሁሉን አጥቼ ኢየሱስን ባገኝ ይሄ ትርፌ ነው ለእኔ ክብሬ ይህ ነው ረቢ ያልኩትን ወዲያ እየጣልኩኝ በፍፁም ልቤ አንተን እየፈለኩኝ የሚታየውን የዓለምን ነገር ትቼ እሮጣለሁ ላገኝ የአንተን ክብር (2x) ሁሉን አግኝቼ አንተን ከማጣ ሁሉን ነገር ኖሮኝ ክብርህ ከሚጐድልብኝ (2x) ሁሉን አጥቼ አንተን ብቻ ባገኝ ይሄ ትርፌ ነው ለእኔ ክብሬ ይህ ነው ሁሉን አጥቼ ኢየሱስን ባገኝ ይሄ ትርፌ ነው ለእኔ ክብሬ ይህ ነው ህልውናህ መገኘትህ ሃልዎትህ ለእኔ ክብሬ ይህ ነው (2x)