Song Lyrics

ነፍሴ ጠዋት ማታ

Endalkachew Hawaz
Egziabher Tilik New
ታስተማምናለህ ጌታዬ እኔም ታመንኩብህ ታስተማምናለህ ብቻህን እኔን ተደገፍኩብህ (2x) ታምኜብሃለሁ ተደግፌሃለሁ ዘመኔን በሙሉ በአንተ እመካለሁ (2x) አዝ፦ ነፍሴ ጠዋት ማታ አንተን ታከብራለች በቀን በሌሊትም ትባርክሃለች (2x) የመኖሬ ትርጉም የሕይወቴ መሰረት አንተ ብቻ ነህ ጌታዬ የጸናሁብህ አለት (2x) ለምን እንደምኖር አውቃለሁ አንተን ስላገኘሁ ለሕይወቴ ትርጉምን ሰጥተሃል ልቤን አሳርፈሃል አርፌብሃለሁ ረክቼብሃለሁ ከቤትህ ጠል ጠጥቼ እኔስ እፎይ ብያለሁ (2x) እግሮቼ በዓለት ላይ ቆመዋል እኔ አልናወጥም አረማመዴም ጸንቶልናል መሰረቴ አይወድቅም የማዕዘን ድንጋይ የሕይወቴ እራስ ብቃቴም ጉልበቴም አንተ ነህ ኢየሱስ (2x) አዝ፦ ነፍሴ ጠዋት ማታ አንተን ታከብራለች በቀን በሌሊትም ትባርክሃለች (2x) የመኖሬ ትርጉም የሕይወቴ መሰረት አንተ ብቻ ነህ ጌታዬ የጸናሁብህ አለት (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection