Song Lyrics

አመልክሃለሁ የእኔ ጌታ

Endalkachew Hawaz
Egziabher Tilik New
በሰማይ አየሁ አንተን የሚመስልህ የለም በምድርም አየሁ አንተን የሚመስልህ የለም ከምድር በታችም አየሁ አንተን የሚመስልህ የለም በልጠህብኛልና መርጬሃለሁ ተሽለኸኛልና ተከትዬሃለሁ በዘመኔ ሁሉ ለአንተ እገዛለሁ ለአንተ እገዛለሁ (4x) አዝ፦ አመልክሃለሁ የእኔ ጌታ አመልክሃለሁ የእኔ ወዳጅ እንደአንተ ያለ ማንም የለም ለእኔ የሚበጅ (2x) አንተን ብቻ ጌታ አመልካለሁ ለአንተ ብቻ ኢየሱስ እገዛለሁ ከአንተ ውጬ ሌላ ሌላ አምላክ የለኝም (4x) ከማን ጋር አንተን ጌታ አስተካክላለሁ ከምን ጋር አንተን ኢየሱስ አመሳስላለሁ ከየትኛውስ ጋራ አንተን አወዳድራለሁ ከብርና ከወርቅ ፍቅርህ በልጦብኛል ከሃጣን ድንኳን ይልቅ ቤትህ ተሽሎኛል ወደአንተ መጠጋቴ ለእኔስ በጅቶኛል (4x) አዝ፦ አመልክሃለሁ (የእኔ ጌታ) የእኔ ጌታ አመልክሃለሁ (የእኔ ወዳጅ) የእኔ ወዳጅ (የእኔ ወዳጅ) እንደአንተ ያለ ማንም የለም ለእኔ የሚበጅ (4x) አንተን ብቻ ጌታ አመልካለሁ ለአንተ ብቻ ኢየሱስ እገዛለሁ ከአንተ ውጬ ሌላ ሌላ አምላክ የለኝም (8x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection