Song Lyrics

በእግዚአብሔር የተወደደ

Endalkachew Hawaz
Egziabher Tilik New
አዝ፦ በእግዚአብሔር የተወደደ በእርሱ ዘንድ ይኖራል (2x) ከትከሻው መሃል ተማምኖ ያድራል (2x) ለሚታመኑበት መታመኛ (ኦሆ መታመኛ) ነውና የሚያኮራ መልካም እረኛ (ኦሆ መልካም እረኛ) እኔም ከጥላው በታች ተጠልያለሁ (ኦሆ ተጠልያለሁ) ፅኑ ክንዱን ተደግፌ አመልከዋለሁ (ኦሆ አመልከዋለሁ) አምላኬ መታመኛዬ በእርሱ እደገፋለሁ የፀና ግንብ ነውና በሥሙ እጓደዳለሁ ገና ነፍሴ ትጠግባለች ከማያልቀው ቸርነቱ በዘይት ሊያለመልመኝ ተክሎኛል እና በቤቱ እርሱን ተማምኜው እኖራለሁ በክንፉቹ ጥላ ስር አርፌያለሁ (2x) አዝ፦ በእግዚአብሔር የተወደደ በእርሱ ዘንድ ይኖራል (2x) ከትከሻው መሃል ተማምኖ ያድራል (2x) ለሚታመኑበት መታመኛ (ኦሆ መታመኛ) ነውና የሚያኮራ መልካም እረኛ (ኦሆ መልካም እረኛ) እኔም ከጥላው በታች ተጠልያለሁ (ኦሆ ተጠልያለሁ) ፅኑ ክንዱን ተደግፌ አመልከዋለሁ (ኦሆ አመልከዋለሁ) የሕይወትን ምንጭ አግኝቼ ከተድላው ፈሳሽ ጠጥቼ ዳግመኛ እኔ አልጠማም ረቻለሁ ለዘለዓለም በብርሃኑ ብርሃን አየሁ ጨለማውም ተሸነፈ ተማምኜ እኖራለሁ ልቤ በእርሱ ስላረፈ እርሱን ተማምኜው እኖራለሁ በክንፉቹ ጥላ ስር አርፌያለሁ (4x) ለሚታመኑበት መታመኛ (ኦሆ መታመኛ) ነውና የሚያኮራ መልካም እረኛ (ኦሆ መልካም እረኛ) እኔም ከጥላው በታች ተጠልያለሁ (ኦሆ ተጠልያለሁ) ፅኑ ክንዱን ተደግፌ አመልከዋለሁ (ኦሆ አመልከዋለሁ) እርሱን ተማምኜው እኖራለሁ በክንፉቹ ጥላ ስር አርፌያለሁ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection