Song Lyrics

ፍቅርህ መልካም ነው

Endalkachew Hawaz
Egziabher Tilik New
ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህ መልካም ነው ለእኔ (2x) አመልክሃለሁ በቀንም በሌሊትም ኢየሱስ መድህኔ (2x) የህይወቴ ጌታ የሕይወቴ ንጉሥ አንተ ብቻ ነህ ኢየሱስ የሕይወቴ ተስፋ የመኖሬ ትርጉም ከአንተ ውጬ ሌላ የለም አዎ ሌላ የለም አንተ ብቻ ነህ ለዘለዓለም አዎ ለዘለዓለም (2x) እስከዛሬ ስኖር በዚህች ምድር አንድም አላየሁም ከአንተ በቀር (2x) ሁሉ ሲይዙት ባዶ ነው ሲጨብጡት እንደ ጉም ነው ኢየሱስ/ጌታ በአንተ ማረፍ ግን እጅግ መታደል ነው (2x) እገባለሁ ወደውስጥ አንተ ወዳለህበት እመጣለሁ በደስታ ለአንተ ልገዛ ጌታ እገባለሁ ወደውስጥ አንተ ወዳለህበት (ወዳለህበት) እመጣለሁ በደስታ ለአንተ ልገዛ ጌታ (እየሰገድኩ) እየሰገድኩ እያመለኩ አንተን አከብራለሁ እየሰገድኩ እያመለኩ (ለአንተ እገዛለሁ) ለአንተ እገዛለሁ እየሰገድኩ (እየሰገድኩ) እያመለኩ (አንተን አነግሳለሁ) አንተን አነግሳለሁ እየሰገድኩ (ጌታዬ) እያመለኩ (ለአንተ እኖራለሁ) ለአንተ እኖራለሁ እየሰገድኩ እያመለኩ (አንተን አንተን) አንተን አከብራለሁ እየሰገድኩ እያመለኩ (ለአንተ እገዛለሁ) ለአንተ እገዛለሁ እየሰገድኩ (እየሰገድኩ) እያመለኩ (ጌታ አነግሻለሁ) አንተን አነግሳለሁ እየሰገድኩ እያመለኩ ለአንተ እኖራለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection