በሃዘን ፈንታ ደስታ በለቅሶም ምትክ ዕልልታ ሁሉንም መልካም አደረገው ክፉውን ለበጐ ቀየረው (2x) አዝ፦ ምን ልበል ሌላማ ሌላማ ምሥጋናዬን/አምልኮዬን ለጌታ ላሰማ (2x) በምሥጋና ስሙን አከብራለሁ (2x) እጅግ እጅግ ብዙ ነው ለእኔ ያደረገው ለእኔ ያደረገው እጅግ እጅግ ብዙ ነው ለእኔ ያደረገው ለእኔ ያደረገው የተዘጋውን ደጅ ከፈተው የነሃሱንም መዝጊያ ሰበረው መወርወሪያዎቹን ቆራርጦ አሳለፈኝ ከፊቴ ወጥቶ አዝ፦ ምን ልበል ሌላማ ሌላማ ምሥጋናዬን/አምልኮዬን ለጌታ ላሰማ (2x) በምሥጋና ስሙን አከብራለሁ (2x) እጅግ እጅግ ብዙ ነው ለእኔ ያደረገው ለእኔ ያደረገው እጅግ እጅግ ብዙ ነው ለእኔ ያደረገው ለእኔ ያደረገው በከበረው ደሙ ቀድሶ መንፈሱን በላዬ አፍሶ ሕይወቴን በፍቅሩ ቀየረው ታሪኬን እንዲህ አሳመረው (2x) አዝ፦ ምን ልበል ሌላማ ሌላማ ምሥጋናዬን/አምልኮዬን ለጌታ ላሰማ (2x) በምሥጋና ስሙን አከብራለሁ በምሥጋና ስሙን አከብራለሁ እጅግ እጅግ ብዙ ነው ለእኔ ያደረገው ለእኔ ያደረገው (4x)