Song Lyrics

ከሁሉ በላይ ነህ ጌታ

Endalkachew Hawaz
Egziabher Tilik New
ሰላምህ በዝቶልኛል አንተን ከአገኘሁ ጀምሮ ሕይወቴ ተለውጧል ተቀይሯል የእኔስ ኑሮ አንተን በመከተሌ ከአንተም ጋር በመሆኔ ተጸጽቼ አላውቅም ጌታ አንተን በማመኔ (5x) አዝ፦ የሕይወትን መንገድ አሳየኽኝ ከፊትህ ጋር ደስታ አጠገብከኝ መልካምነትህን አበዛህ በዘመኔ ከሁሉም በላይ ሆንክልኝ መድህኔ (2x) ከሁሉ በላይ ነህ ጌታ ከሁሉ በላይ ከሁሉ በላይ ነህ ኢየሱስ ከሁሉ በላይ (2x) የጐደለብኝ የለም ሁሉ ሞላልኝ እንጂ በረከት እንደሁ አያልቅም ከአንተ ቤት ከአንተ ደጅ የሰላም አለቃ ሆይ የሰላሜ ምንጭ ነህ ማንም አይመጥንህም ከምርጦች ሁሉ ልዩ ነህ (5x) አዝ፦ የሕይወትን መንገድ አሳየኽኝ ከፊትህ ጋር ደስታ አጠገብከኝ መልካምነትህን አበዛህ በዘመኔ ከሁሉም በላይ ሆንክልኝ መድህኔ (2x) ከሁሉ በላይ (በላይ በላይ) ነህ ጌታ ከሁሉ በላይ ከሁሉ በላይ (ከሁሉ በላይ) ነህ ኢየሱስ ከሁሉ በላይ (ጌታ) (2x) ከምን ጋር ላወዳድርህ ከማን ጋር ላስተካክልህ ከሚታይ ከማይታየው ከሁሉ ትበልጣለህ ከሁሉ ትበልጣለህ (አው ከሁሉ) ከሁሉ ትሻላለህ (ሁሁ) እድል ፈንታዬ ጌታ (እድል ፈንታዬ ጌታ) ለዘለዓለም ምርጫዬ ነህ (5x) አዝ፦ የሕይወትን መንገድ አሳየኽኝ ከፊትህ ጋር ደስታ አጠገብከኝ መልካምነትህን አበዛህ በዘመኔ ከሁሉም በላይ ሆንክልኝ መድህኔ (2x) ከሁሉ በላይ (ኦ አንተ ከሁሉ በላይ) ነህ ጌታ ከሁሉ በላይ (ኢየሱስ ከሁሉ በላይ) ከሁሉ በላይ (ቃልህ ከሁሉ በላይ) ነህ ኢየሱስ ከሁሉ በላይ (ክብርህ ከሁሉ በላይ መንግሥትህ ከሁሉ በላይ) ከሁሉ በላይ (ሥጋህ ከሁሉ በላይ) ነህ ጌታ ከሁሉ በላይ (ፍቅርህ ከሁሉ በላይ) ከሁሉ በላይ (ኦ አንተ ከሁሉ በላይ) ነህ ኢየሱስ ከሁሉ በላይ (በላይ በላይ) (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection