Song Lyrics

አምላኬ መታመናዬ ነው

Endalkachew Hawaz
Egziabher Tilik New
አዝ፦ አምላኬ መታመኛዬ ነው አምላኬ መሸሸጊያዬ ነው (2x) በልዑል መጠጊያ እኖራለው ሁሉን በሚችል ጥላ ስር አድራለሁ እግዚአብሔር ለእኔ መታመኛዬ ነው እግዚአብሔር ለእኔ መሸሸጊያዬ ነው መሸሸጊያዬ ነው (2x) ከክንፎቹ በታች እተማመናለሁ የሌሊቱን ግርማ መቼ እፈራለሁ (2x) እውነት እንደጋሻ ዙሪያዬን ከቦኛል በመንገዴ ሁሉ ጌታ ይመራኛል አዝ፦ አምላኬ መታመኛዬ ነው አምላኬ መሸሸጊያዬ ነው (2x) በልዑል መጠጊያ እኖራለው ሁሉን በሚችል ጥላ ስር አድራለሁ እግዚአብሔር ለእኔ መታመኛዬ ነው እግዚአብሔር ለእኔ መሸሸጊያዬ ነው መሸሸጊያዬ ነው (2x) በመከራዬ ቀን ከእኔ ጋራ ሆኖ ማዳኑን አሳየኝ ምህረቱን አግንኖ (2x) በጠራሁት ጊዜ ፈጥኖ መለሰልኝ እንዳልሰናከል በእጆቹ አነሳኝ (2x) አዝ፦ አምላኬ መታመኛዬ ነው አምላኬ መሸሸጊያዬ ነው (2x) በልዑል መጠጊያ እኖራለው ሁሉን በሚችል ጥላ ስር አድራለሁ እግዚአብሔር ለእኔ መታመኛዬ ነው (2x) እግዚአብሔር ለእኔ መሸሸጊያዬ ነው (2x) እግዚአብሔር ለእኔ መታመኛዬ ነው (2x) እግዚአብሔር ለእኔ መሸሸጊያዬ ነው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection