Song Lyrics

እግዚአብሔር ትልቅ ነው

Endalkachew Hawaz
Egziabher Tilik New
ትልቅ ነው እግዚአብሔር ትልቅ ነው ለክብሩ መጨረሻ የሌለው ትልቅ ነው እግዚአብሔር ትልቅ ነው ለኃይሉ መጨረሻ የሌለው (2x) እዘምራለሁ ለእርሱ እቀኛለሁ የክብሩን ብዛት ግርማውን እያየሁ እዘምራለሁ ለእርሱ እቀኛለሁ የኃይሉን ችሎት ብርታቱን እያየሁ (2x) በጠባባ አይምሮዬ አልችልም ልገምተው እስካሁን ካወቅሁት በላይ እግዚአብሔር እጅግ ትልቅ ነው እንኳን ማንነቱ ቀርቶ ስራውም አይመረመር ከተባለው ሁሉ ያልፋል ይበልጣል የአምላኬ ክብር በምን ቋንቋ ስለእርሱ ልናገር በምን ቋንቋ ስለእርሱ ልመስክር ቃላት ባጣም እንዲያው ላመስግነው አምልኮዬ እርሱን ባይመጥነው (2x) ግርማው እጅግ የሚያስፈራ ታላቅ ስሙ የገነነ ደግሞ መሃሪ ቸር አምላክ የፍቅር ጌታ የሆነ ብርሃንን ተጐናጽፎ ማደሪያውን በክብር የሞላ እንደእግዚአብሔር ያለ አምላክስ የታለ ሌላ ትልቅ/ታላቅ ነው እግዚአብሔር ትልቅ/ታላቅ ነው ለክብሩ መጨረሻ የሌለው ታልቅ ነው እግዚአብሔር ታልቅ ነው ለኃይሉ መጨረሻ የሌለው (2x) እዘምራለሁ ለእርሱ እቀኛለሁ የክብሩን ብዛት ግርማውን እያየሁ እዘምራለሁ ለእርሱ እቀኛለሁ የኃይሉን ችሎት ብርታቱን እያየሁ (3x) በምን ቋንቋ ስለእርሱ ልናገር በምን ቋንቋ ስለእርሱ ልመስክር ቃላት ባጣም እንዲያው ላመስግነው አምልኮዬ እርሱን ባይመጥነው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection