አዝ፦ በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም ሥሙንም ጠርቼ እኔ አላጣሁም ከመልካም ነገር ፈጽሞ አልጐደልኩም (2x) ውድቀቴን ሲጠብቅ አሁንም ያ ክፉ አታልፊውም ሲለኝ ቀኖቹም ሲከፉ የነፍሴ እረኛ ኢየሱስ ደረሰና እኔን አሻገረኝ ታሪክ ለወጠና አዝ፦ በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም ሥሙንም ጠርቼ እኔ አላጣሁም ከመልካም ነገር ፈጽሞ አልጐደልኩም (2x) ጠላት ሲያስለቅሰኝ ሸለቆ እያሳየ እግዚአብሔር ከሠማይ ሰምቶ ዘንበል አለ እንባዬን አብሶ ደስታን አለበሰኝ ለልቤ መጽናናት በእርሱ ላይ ሆነልኝ አዝ፦ በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም ሥሙንም ጠርቼ እኔ አላጣሁም ከመልካም ነገር ፈጽሞ አልጐደልኩም (2x) ገበናዬን ሸፊኝ ሚስጥር ተካፋዬ ጉድለቴን ሞላልኝ በእርሱ በጌታዬ በሠማዩ ስፍራ በመንፈስ ባርኮኛል የመንግሥቱ ወራሽ ርስቱ አድርጐኛል አዝ፦ በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም ሥሙንም ጠርቼ እኔ አላጣሁም ከመልካም ነገር ፈጽሞ አልጐደልኩም (2x) ሰምቶ የሚመልስ አይቶ የሚራራ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለምና ታዲያ ለዚህ ጌታ ላብዛለት ምሥጋና ክብር ያገኘሁት በአምላኬ ነውና አዝ፦ በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም ሥሙንም ጠርቼ እኔ አላጣሁም ከመልካም ነገር ፈጽሞ አልጐደልኩም (2x)