Song Lyrics

ወድጄ ፈቅጄ

Elsa Getachew
Yaltebekutin Kal
ወድጄ ፈቅጄ እኔ የማመልክህ የአባቶቼ አምላክ ኢየሱስ አንተ ነህ እግዚአብሔር ብርሃኔ መድኃኒቴ ሆነህ እዚህ የመድረሻ መታመኛዬ ነህ ሃ ሃሌሉያ (4x) አንተን እያመለኩ ጉዞ ከጀመርኩኝ በትንሹ ዕድሜዬ ቤትህ ከመጣሁኝ ፍቅር እንጂ ከአንተ ክፉን አላየሁም ለማምለክ ፈቅጄ በዚህ ተረታሁኝ ተባረክ አሃሃ ተመስገን ኦሆሆ (2x) በሕይወቴ ትልቅ ስፍራ የምሰጠው ለአንተ ነው በኑሮዬ ሰፊ ቦታ የምሰጠው ለአንተ ነው (2x) ጌታዬ ለአንተ ነው አምላኬ ለአንተ ነው ንጉሤ ለአንተ ነው ሕይወቴ በአንተ ነው ሃ ሃሌሉያ (4x) ፍቅር ነህ የእኔ ጌታ ፍቅር ነህ ፍቅር ነህ ኢየሱሴ ፍቅር ነህ (2x) ሃ ሃሌሉያ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection