Song Lyrics

አለኝ የምለው

Elsa Getachew
Yaltebekutin Kal
አዝ፦ አለኝ የምለው በዚህ በምድር ላይ አንድም የለኝም ጌታ ከአንተ በላይ አልችልምና ያለአንተ መኖር መንፈስህ ሁሉ በሕይወቴ ይኑር (2x) ቁስለኛውን ልቤን የሚጠግነው የነፍሴን ህመም የሚፈውሰው መንፈስህ ነው ተስፋ ያደረኩት በምድር ያለውን አይደለም ያየሁት የተሰበረውን አንተ የምትሻውን መስዕዋት አድርገህ የምታሸተውን ይህን መንፈስ ስጠኝ እለም ጸሎቴ ይህ ነው እለምንሃለሁ አንተን የሚፈልግ ልብን ፍጠርልኝ የቀናውን መንፈስ በውስጤ አድስልኝ ባክህን ጌታ ከፊትህ አትጣለኝ ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ አትውሰድብኝ (3x) አዝ፦ አለኝ የምለው በዚህ በምድር ላይ አንድም የለኝም ጌታ ከአንተ በላይ አልችልምና ያለአንተ መኖር መንፈስህ ሁሉ በሕይወቴ ይኑር (2x) መንገዴ ይሄ ነው ብሎ ያሳየኝ የሕይወቴ መሪ ለእኔ የሆነልኝ መንፈስህ ብቻ እረፍትን የሰጠኝ ከመከራ ስጋት እኔን ያሳረፈኝ ልክ እንደነኤልሳ እንደ ኤልያስ ልቤ ታዛዥ ይሁን ለአንተ መንፈስ እንደ ወደድክ አርፈህ በእኔ እንድትሰራ ሕይወቴን ሰጠሁህ ጌታ ሆይ አደራ ብርና ወርቅ ለእኔ ሰላም አልሆነኝም ሃብትና ንብረትም እረፍት አልሰጠኝም ውስጣዊው እርካታ የልቤ ደስታ አንተ ነህ የሰጠኸኝ ክበር የእኔ ጌታ ክበር ክብር የእኔ ጌታ (2x) አዝ፦ አለኝ የምለው በዚህ በምድር ላይ አንድም የለኝም ጌታ ከአንተ በላይ አልችልምና ያለአንተ መኖር መንፈስህ ሁሉ በሕይወቴ ይኑር (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection