Song Lyrics

ኧረ አመስግኑልኝ

Elsa Getachew
Yaltebekutin Kal
ማህጸኗ ቢደርቅ ይዟት ተስፋዋ ተሟጦ ልጅ መውለድ ቢያቅታት የአብርሃም አምላክ መቼ አረጀና ይወለዳል ይስሃቅ እርሱ ብሏልና (2x) አዝ፦ ኧረ አመስግኑልኝ ይህን ጀግና ጌታ ከፍ ይበል ይባረክ ይንገሥ በዕልልታ እርሱ ብቻ እኮ ነው የእኛስ አምላካችን ሲሰራ ስላየን ዛሬም በሕይወታችን እርሱ ብቻ እኮ ነው የእኛስ አምላካችን ሲሰራ ስላየን ዛሬም በሕይወታችን (2x) አብርሃም ቢያረጀም ሳራም ብትደካክም ሁኔታውን አይተው የማይሆን ቢመስልም ለጌታ ምን አቅቶት ምን ተስኖት ያውቃል ይስሃቅን ሰጥቷቸው አስደንቋቸዋል (2x) አዝ፦ ኧረ አመስግኑልኝ ይህን ጀግና ጌታ ከፍ ይበል ይባረክ ይንገሥ በዕልልታ እርሱ ብቻ እኮ ነው የእኛስ አምላካችን ሲሰራ ስላየን ዛሬም በሕይወታችን እርሱ ብቻ እኮ ነው የእኛስ አምላካችን ሲሰራ ስላየን ዛሬም በሕይወታችን (2x) የሚያስፈልግህን በጊዜው ያደርጋል ታምነህ ከተቀመጥክ ቃሉንም ያከብራል አድራሻህን አድርገው ከዙፋኑ ሥር ፈጥኖ ይረዳሃል ታማኝ ነው እግዚአብሔር አድራሻሽን አድርጊው ከዙፋኑ ሥር ፈጥኖ ይረዳሻል ታማኝ ነው እግዚአብሔር አዝ፦ ኧረ አመስግኑልኝ ይህን ጀግና ጌታ ከፍ ይበል ይባረክ ይንገሥ በዕልልታ እርሱ ብቻ እኮ ነው የእኛስ አምላካችን ሲሰራ ስላየን ዛሬም በሕይወታችን እርሱ ብቻ እኮ ነው የእኛስ አምላካችን ሲሰራ ስላየን ዛሬም በሕይወታችን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection