አዝ፦ አካሄዴን ጌታ እንደቃልህ አቅና ፀጋህ ይደግፈኝ ደካማ ነኝና ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው እንክርዳድን ከስንዴ የሚለይ ነው (2x) ከማር ከወለላ ሁሉ የሚጣፍጠው ከነገሮች ሁሉ እጅጉን የሚበልጥ አለኝ የሕይወት ቃል የተከበረው ጌታም አጽንቶታትል የማይሻር ነው አዝ፦ አካሄዴን ጌታ እንደቃልህ አቅና ፀጋህ ይደግፈኝ ደካማ ነኝና ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው እንክርዳድን ከስንዴ የሚለይ ነው (2x) በሕይወቴ ዘመን አንተን እንዳመልክህ ጌታ በኑሮዬ ቃልህን አብራልኝ ከአመጸኛ ከንፈር ከሸንጋይ አንደበት ጌታ ሆይ ጠብቀኝ እንደ ቃልህ እንድኖር አዝ፦ አካሄዴን ጌታ እንደቃልህ አቅና ፀጋህ ይደግፈኝ ደካማ ነኝና ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው እንክርዳድን ከስንዴ የሚለይ ነው (2x) ባክህ ተናገረኝ ዝምም አትበለኝ ቃልህን አብራልኝ ከፊትህ አትጣለኝ ጌታ ሆይ ቃልህ ተስፋ አደርገዋለሁ በናፍቆት በጉጉት እጠባበቃለሁ አዝ፦ አካሄዴን ጌታ እንደቃልህ አቅና ፀጋህ ይደግፈኝ ደካማ ነኝና ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው እንክርዳድን ከስንዴ የሚለይ ነው (2x)