በዓለም ተጥዬ ዋጋም ሳይኖረኝ በሰውም ተንቄ ስፍራንም ሳላገኝ ቃሉን ሲያወጣ ከማደሪያው ቦታ ታላቅም ሠራዊት አድርጐኛል ጌታ (2x) ሕይወቴን ሊጐዳ ዝቶብኝ ጠላቴ እግዚአብሔር አዳነኝ ጥሶ ገብቶ ቤቴ እኔም አመልካለሁ ይህን ታላቅ ጌታ አውጥቶኛልና ከጭንቅ ከመከራ አዝ፦ የውለታው ብዛት ሳስብ ይገርመኛል ጌታ ለእኔ ያደረገው እጅግ ይደንቀኛል (2x) ምኔን አይተህ ልበል ምኔ ስቦት ይሆን እንዲህ የወደደኝ እንዲሁ በፍቅሩ የእራሱ አደረገኝ ከጠላት መንጋጋ ፈልቅቆ አስመለጠኝ ከዓለም ለይቶ ለእራሱ አደረገኝ አይተወኝም እርሱ መቼም አይረሳኝም በፍቅሩ እኔን ገዝቶ ልቤን ማርኮ አምነዋለሁ እርሱን ዘለዓለማዊ ነው አይጥለኝም ሁሌ ታማኝ ወዳጄ ነው አዝ፦ የውለታው ብዛት ሳስብ ይገርመኛል ጌታ ለእኔ ያደረገው እጅግ ይደንቀኛል (2x) ምኔን አይተህ ልበል ምኔ ስቦት ይሆን እንዲህ የወደደኝ እንዲሁ በፍቅሩ የእራሱ አደረገኝ ከጠላት መንጋጋ ፈልቅቆ አስመለጠኝ ከዓለም ለይቶ ለእራሱ አደረገኝ ደግፎ ያቆመኝ እኔን በምህረት የማውቀው ጌታን ነው ደግሞም በቸርነት መጣ እኔንም አይቶ ያነሳኝ እርሱ ነው ዛሬም ቢሆን ነገ በእርሱ እታመናለሁ አዝ፦ የውለታው ብዛት ሳስብ ይገርመኛል ጌታ ለእኔ ያደረገው እጅግ ይደንቀኛል (2x) ምኔን አይተህ ልበል ምኔ ስቦት ይሆን እንዲህ የወደደኝ እንዲሁ በፍቅሩ የእራሱ አደረገኝ ከጠላት መንጋጋ ፈልቅቆ አስመለጠኝ ከዓለም ለይቶ ለእራሱ አደረገኝ