አዝ፦ በዘሬ አይግባ ያልኩት ከመንደሬ ገፍቼ ያወጣሁት እርሱ ነው ነፍሴን ያዳንው በሞት መሃል የደረሰው ቀንበሬን የሰበረልኝ ኢየሱስ ይባረክልኝ በጎነቱ ሲነገረኝ ማዳኑ መቼ ማረከኝ ጆሮዬን በእጄ ዘግቼ ኢየሱስን አይን ላፈር አልኩኝ መራቡን ያላወቀ ሰው እንዴት እንጀራ አንስቶ ይብላ ኋላ ግን ሲሞረሙረው ይሻዋል ቀድሞ እንዳልበላ አዝ፦ በዘሬ አይግባ ያልኩት ከመንደሬ ገፍቼ ያወጣሁት እርሱ ነው ነፍሴን ያዳንው በሞት መሃል የደረሰው ቀንበሬን የሰበረልኝ ኢየሱስ ይባረክልኝ መስቀሉን በጀርባው ጭኜ ጦሬን መዝዤ ጨክኜ ጎልጎታ ድረስ ወሰድኩት እጁን ቸንክሬ ሰቀልኩት ከአዘነለት ሰው ይልቅ ምህረቱ ለኔ ቀደመ ሚያደርገውን አያውቅምና አባት ሆይ ማረው ተባለ አዝ፦ በዘሬ አይግባ ያልኩት ከመንደሬ ገፍቼ ያወጣሁት እርሱ ነው ነፍሴን ያዳንው በሞት መሃል የደረሰው ቀንበሬን የሰበረልኝ ኢየሱስ ይባረክልኝ ኃጢያቴ በዝቶ በደጄ ሊገድለኝ ሲጥር ሲያደባ ባፈሰስኩበት ደሙ አጥቦ ሊያነፃኝ ቃል ገባ አጥንቴ ደቆ ስቆዝም አይዞህ የሚል ሰው ሲጠፋ ኢየሱስ ግን ለእኔ ደረሰ ያኔ በእጄ የተገፋ አዝ፦ በዘሬ አይግባ ያልኩት ከመንደሬ ገፍቼ ያወጣሁት እርሱ ነው ነፍሴን ያዳንው በሞት መሃል የደረሰው ቀንበሬን የሰበረልኝ ኢየሱስ ይባረክልኝ አጥላልቼው ከወደደ ለሰቀልኩት ከማለደ ምን ይሆንለት ምላሹ እንደ ስራዬ ካላዋረደኝ ኢየሱሴ አድነኝ ስለው ያኔ ምን አረክ አላለም እንደ እርሱ ትሁት ቸር የለም ስሙ ይባረክ ዘላለም