Song Lyrics

ተመስገን

Elias Abte
Yemites Tuafen Alatefahim
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ተመስገን ተመስገን ተመስገን በሰማይ ተመስገን በምድር ተመስገን ማን አለኝ ከአንተ ሌላ የህይወቴ ከለላ ማን አለኝ ከአንተ ወዲያ ተመስገን ሃሌሉያ በህይወቴ የሞላው የሃጥያት ነቀርሳ ለሞት እስኪያስጨንቅ እጅጉን ሲበዛ የጣር ጩኸቴን ሰምቶ ከሰማይ ወረደ ነፍሴን ሰላም ሰጣት ሞቴን አስወገደ የማይገባኝን ሰማያዊ ጥሪ የጠራኝ ሳያንሰው አረገኝ መስካሪ የምህረቱን ብዛት በነፍሴ አሳየኝ በህይወት ስላኖረኝ ክብርን እሰዋለሁኝ ተመስገን ተመስገን ተመስገን ተመስገን ተመስገን ተመስገን በሰማይ ተመስገን በምድር ተመስገን ማን አለኝ ከአንተ ሌላ የህይወቴ ከለላ ማን አለኝ ከአንተ ወዲያ ተባረክ ሃሌሉያ በበረታ ሃዘን መንፈሴ ተሰብሮ መጽናናት ሲርቀኝ ዘመናትን ቆጥሮ በድካም በዝለት በወደኩት ስፍራ ውዴ ኢየሱስ መጣ በስሜ ተጣራ እንባዬን አበሰ አይኖቼን ከፈተ ለደቀቀው ልቤ መጽናናትን ሰጠ እንደርሱ ሚሆነኝ አላገኘሁምና በፊቱ እሰዋለሁ ለስሙ ምስጋና ተመስገን ተመስገን ተመስገን ተመስገን ተመስገን ተመስገን በሰማይ ተመስገን በምድር ተመስገን ማን አለኝ ከአንተ ሌላ የህይወቴ ከለላ ማን አለኝ ከአንተ ወዲያ ተባረክ ሃሌሉያ ቁስሌን በዘይት ስታሽ ድርቀቴን ስትፈውስ ስብራቴን ስትጠግን አንባዬን ስታብስ ጠያቂዎቼ ብዙ አስታማሚዎቼ ከኔ እንደማይሻሉ አየሁኝ በአይኖቼ መጽናናት ሃይልንም ከእኔ ጠበቁ ከአፌ በወጣው ቃል ተፈውሰው ሳቁ ክብሬም ታድሶልኝ በትሬም ለምልሞ ደስታዬን ለማየት ሰዉ ተሽቀዳድሞ ተመስገን ተመስገን ተመስገን ተመስገን ተመስገን ተመስገን በሰማይ ተመስገን በምድር ተመስገን ማን አለኝ ከአንተ ሌላ የህይወቴ ከለላ ማን አለኝ ከአንተ ወዲያ ተባረክ ሃሌሉያ ብላቴናነቴ ተንቆ ወንጭፌ ከጎልያድ አንደበት እርግማን ጠግቤ ቅናቱ ሲበላኝ የስምህ መሰደብ ፈተና ሆኖ ፊቴ በእንባ ሲታጠብ በእኔ ላይ የአለው የመንፈስህ ብርታት በክቡር ስምህ ስልጣን ጉልበትህ ሲገለጥ ያነሳሁት ድንጋይ መቼ የዋዛ ሆነ ጠላቴን አድቅቆ ስምህን አስከበረ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection