አዝ፦ ቤትህ በተሰራ ጊዜ የድንጋይ ጩኸት አልነበረም መራጃው ከቶ አልተንኳኳም በተሸለሙ ድንጋዮች የተሰራ ማን ታወከ መች ሆነ ተራራ ዛሬ ግን ያለመረዳት እሩጫ ሆነ በሰባራ ገል ቤትህ ተሰራ ተከናወነ ኡ እኔስ ፈራሁ ጩኸቱ ሲበዛ አውቄህ ልኑር ሰብስበኝ በቃልህ ጣዛ ኡ እኔስ ፈራሁ የኔ ጌታ እራሴን ልየው ከጠዋት እስከማታ ድንጋዩ እንዳይታይ በዝግባ ሲለበጥ ዝግባው ባማረ ወርቅ ሲያጌጥ መስራትም መሰራትም ያኔ ነበረ ይታያልም ክብር ሲገለጥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ይፈርሳ ተባለ መች ቀረ ይኸው አሁን ሆነ ወንድም ከወንድሙ ጋራ ሳይጣበቅ ፡ በጩኸት ሞቀ ቤቱ ጋለ አዝ፦ ቤትህ በተሰራ ጊዜ የድንጋይ ጩኸት አልነበረም መራጃው ከቶ አልተንኳኳም በተሸለሙ ድንጋዮች የተሰራ ማን ታወከ መች ሆነ ተራራ ዛሬ ግን ያለመረዳት እሩጫ ሆነ በሰባራ ገል ቤትህ ተሰራ ተከናወነ ኡ እኔስ ፈራሁ ጩኸቱ ሲበዛ አውቄህ ልኑር ሰብስበኝ በቃልህ ጣዛ ኡ እኔስ ፈራሁ የኔ ጌታ እራሴን ልየው ከጠዋት እስከማታ ዘሩ በመንገድ ዳር ወድቆ ሲለቀም በጭንጫ ላይ ያለው ሲከስም ግማሹ በእሾህ መሃል ሲታነቅ ባለ ፍሬ ጠፍቶ ሲደርቅ ከወርቅ ይልቅ የሚፈተነው እምነት በዝማሬ ተመስሎ ጠፋ ከነኣን ላይገባ በኢያሪኮ ዙሪያ ሞልቷል መለከት የሚነፋ አዝ፦ ቤትህ በተሰራ ጊዜ የድንጋይ ጩኸት አልነበረም መራጃው ከቶ አልተንኳኳም በተሸለሙ ድንጋዮች የተሰራ ማን ታወከ መች ሆነ ተራራ ዛሬ ግን ያለመረዳት እሩጫ ሆነ በሰባራ ገል ቤትህ ተሰራ ተከናወነ ኡ እኔስ ፈራሁ ጩኸቱ ሲበዛ አውቄህ ልኑር ሰብስበኝ በቃልህ ጣዛ ኡ እኔስ ፈራሁ የኔ ጌታ እራሴን ልየው ከጠዋት እስከማታ እርስ በእርሳቸው የማይገላመጡ ለእግዚአብሔር ክብር ሚሮጡ አገልጋዮች የሉም ራሳቸውን የካዱ ማይነቀፉ የተለወጡ ፍርድን ከራሱ ቤት ይጀምራልና ፡ ወደ ህያው ድንጋይ እናቅና በታቦት ብቻ እልልታን ከማቅለጥ ኢየሱስን እንምሰል እንደግ