Song Lyrics

ክብርን እንሰጣለን

Elias Abte
Yemites Tuafen Alatefahim
ልባችንን ከእጃችን ጋር በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር እናነሳለን ክብርንም እንሰጣለን እናመልካለን በፊቱ እንሰግዳለን ሰማይ ዝፋንህ ነው መቀመጫህ ምድርም ለእግሮችህ መርገጫህ ለትልቅነትህ ወሰን ነህ የሌለህ ሰማያትንም በስንዝር የለካህ እንሰግዳለን ለአንተ ክብር ይሁን ጌታ ልባችንን ከእጃችን ጋር በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር እናነሳለን ክብርንም እንሰጣለን እናመልካለን በፊቱ እንሰግዳለን እስትንፋሽን ለሙታን ትሠጣለህ በባዶ ሸለቆ ውሃን ትሞላለህ ጥበብህን ችሎታህን ማን ይለካዋል ያልነበርን እንደምታኖር አውቀዋል ከፍ ያልከው ጌታ ክብር ይገባሃል ልባችንን ከእጃችን ጋር በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር እናነሳለን ክብርንም እንሰጣለን እናመልካለን በፊቱ እንሰግዳለን እንዲበላ እንዲጠጣ ለራሱ እንዲኖር ብቻ አልነበርም ሰውን በእጅህ መስራት እንዲያመልክህ በታላቅነት እንዲያከብርህ መሆኑን ተረድቻለሁ እኔን መፍጠርህ ታላቅ ነህ አንተ ጌታ ሆይ ክብር ይሁንልህ ልባችንን ከእጃችን ጋር በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር እናነሳለን ክብርንም እንሰጣለን እናመልካለን በፊቱ እንሰግዳለን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection