Song Lyrics

ኃይልህ በድካሜ ሲገለጥ

Elias Abte
Yemites Tuafen Alatefahim
አዝ፦ ኃይልህ በድካሜ ሲገለጥ ሲገለጥ ሲገለጥ በአንተ አለፍኩት ይህን ዘመኔን ይህን ኑሮዬን አገልግሎቴን መድኃኒቴ ክብር ይሁንህ ጉልበቴ ኃይልህ በድካሜ ሲገለጥ ሲገለጥ ሲገለጥ ጠላቴን መታሁት አሸነፍኩት አዋረድኩት አሳፈርኩት መድኃኒቴ ክብር ይሁንህ ጉልበቴ ከባርነት ቤት ስታላቅቀኝ ቀንበሬን ሰብረህ ስትጥልልኝ ባህሩን በክንድህ ስትከፍልልኝ ጭቃው ሳይነካኝ ስታሻግረኝ ጫማዬ አልቆ በእግሬ ሳልሄድ ጨርቄም ከገላዬ ሳይቀደድ በበለዓም ፊት ሞገስ ለድንኳኔ አጎናጸፍከኝ ክበር መድህኔ ንገሥ መድህኔ አዝ፦ ኃይልህ በድካሜ ሲገለጥ ሲገለጥ ሲገለጥ በአንተ አለፍኩት ይህን ዘመኔን ይህን ኑሮዬን አገልግሎቴን መድኃኒቴ ክብር ይሁንህ ጉልበቴ ኃይልህ በድካሜ ሲገለጥ ሲገለጥ ሲገለጥ ጠላቴን መታሁት ፡midnight አሸነፍኩት አዋረድኩት አሳፈርኩት መድኃኒቴ ክብር ይሁንህ ጉልበቴ ቆሜያለሁ ሚልን የሚያፍገመግም ብርቱ ነኝ ያለውን የሚያደክም ይሄ ክፉ ቀን ፍጹም ሲያሯሩጥ በወዳጁ ፊት ሲያለማምጥ ክረምትም በጋም ለማይሞላው ሆድ ሗላውን ሳያውቅ ሰው ሲካካድ ሁሉን አራግፋ ያየችህ ነፍሴን በድንቅ አኖርካት ክበር ኢየሱሴ ንገስ ኢየሱሴ አዝ፦ ኃይልህ በድካሜ ሲገለጥ ሲገለጥ ሲገለጥ በአንተ አለፍኩት ይህን ዘመኔን ይህን ኑሮዬን አገልግሎቴን መድኃኒቴ ክብር ይሁንህ ጉልበቴ ኃይልህ በድካሜ ሲገለጥ ሲገለጥ ሲገለጥ ጠላቴን መታሁት አሸነፍኩት አዋረድኩት አሳፈርኩት መድኃኒቴ ክብር ይሁንህ ጉልበቴ ጉስቁልናዬን እያስቆጠረኝ ይሄ ጠላቴ ሲያስለቅሰኝ የቀራዮን ደም አንዳልዘነጋ አይኔን አቅንቼ አንተን ፍለጋ ጉስቁልናዬን በብልጽግና ከላይ ከአርያም ሞላህና ስት ሸላልመኝ እፍረት ሆነለት አበሳውንም አበዛህበት ጠላቴን ክበር የኔ አባት አዝ፦ ኃይልህ በድካሜ ሲገለጥ ሲገለጥ ሲገለጥ በአንተ አለፍኩት ይህን ዘመኔን ይህን ኑሮዬን አገልግሎቴን መድኃኒቴ ክብር ይሁንህ ጉልበቴ ኃይልህ በድካሜ ሲገለጥ ሲገለጥ ሲገለጥ ጠላቴን መታሁት አሸነፍኩት አዋረድኩት አሳፈርኩት መድኃኒቴ ክብር ይሁንህ ጉልበቴ በአንዳንዱ ቀን ውስጤን ሲከፋው የነፍሴን ጓዳ ባዶ ነህ ሲለው መታጠቂያዬን ማጥበቅ ሲያቅተኝ ታናሽነቴ ሚናቅ ሲመስለኝ ደመናን ቀዶ ክንድህ ይወርዳል መወርወሪያውን ይቆራርጣል ሥራዬን ሰርተህ ስትዋጋልኝ እጆቼን በአፌ ላይ አስጫንከኝ ተመስገንልኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection