አዝ፦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ የቁጣቸው ግለት በላይህ በረደብህ ምን ልበል ታዲያ ውዴ ምንስ ልክፈልህ በአንተ አረፈች ነፍሴ ለዘላለም ታመስግንህ ያ አስፈሪው ግርማህ ለአንዳፍታ ተቀይሮ ጌታነትህ ክብር በባርነት ተመንዝሮ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ አራስህን አድን ሲሉህ የእኔን ቂም በእንተ በመስቀል ሲወጡ ነፍሴ ወጣች ከእስራቱ አዝ፦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ የቁጣቸው ግለት በላይህ በረደብህ ምን ልበል ታዲያ ውዴ ምንስ ልክፈልህ በአንተ አረፈች ነፍሴ ለዘላለም ታመስግንህ የሰው አንቆቅልሽ በአንተ ዘንድ ምላሽ ሲያገኝ ለተገፊዎቹም ችሎት ቀርበህ ስትል ይግባኝ በአንተ መገፋት ግን ሰማይ ምድር ዝም ሲሉ ሃይልህ አስኪገለጥ አጅግ ቢያቃልሉህ በክንድህ ሲዖል ተጣሉ አዝ፦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ የቁጣቸው ግለት በላይህ በረደብህ ምን ልበል ታዲያ ውዴ ምንስ ልክፈልህ በአንተ አረፈች ነፍሴ ለዘላለም ታመስግንህ የክፋቴ ብዛት በሰው አፍ መርገም ሆኖ ወሬ ለሚሰማ ለሚያይም አይን አስጨፍኖ በሰፈሬ ስታልፍ ያንን ስድቤን ስትሸከም በቁጣው ስትደርቅ ነፍሴን ለማለምለም ከፍ በል ለዘለዓለም አዝ፦ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ የቁጣቸው ግለት በላይህ በረደብህ ምን ልበል ታዲያ ውዴ ምንስ ልክፈልህ በአንተ አረፈች ነፍሴ ለዘላለም ታመስግንህ ቆሞ በምድር ላይ ከህያዋን መቀላቀል በሚመጣውም አለም ብቤትህ አኔን ስትቀበል ከዚያም አልፎ የጓዳዬ መከራ ሲረሳ ከአንተ የተነሳ ቀረ ያ አበሳ ክበር የይሁዳ አንበሳ