Song Lyrics

አብርሃም ቢያረጅ አታረጅም

Elias Abte
Yemites Tuafen Alatefahim
ሽምግልናዬን ጌታዬ ሆይ አድስ የሕይወቴን ጎዳና ወደ ተስፋህ መልስ በእምነቴም በኑሮ እንዲሁ አርጅቻለሁ ዛሬ በአንተ መታደስን እሻለሁ ለአብርሃም አከብርሃለሁ ዘርህን አበዛለሁ ብለህ በተስፋ ስትጠራው ዘሩን ልታበዛው ተስፋው ሲዘገይ ከሳራ ጋር አብሮ ተማከረ እርጅናው ሲዘምር ከተስፋው ቃል ጥቂት ፈቀቅ አለ አብርሃም ቢያረጅ አታረጅም ሽምግልና አንተን አያውቅ ህም እንደተናገርክ ታደርጋለህ ሸለቆዬን በውሃ ትሞላለህ ጥንትም ብርቱ ነህ ዛሬም ብርቱ ነህ ነገም ትኖራለህ ጥንትም ብርቱ ነህ ዛሬም ብርቱ ነህ ነገም ትሰራለህ ሽምግልናዬን ጌታዬ ሆይ አድስ የህይወቴን ጎዳና ወደ ተስፋህ መልስ በእምነቴም በኑሮ እንዲሁ አርጅቻለሁ ዛሬ በአንተ መታደስን እሻለሁ በሕይወት በኑሮ ጌታዬ ሆይ እጅግ ደክሜያለሁ ፍሬ ሳይኖረኝ ዘመናትን ብዙ አሳልፌያለሁ ሃይሌ አልቆብኝ ጉልበቶቼ እየተብረከረኩ አለኝ ያልኩትን የያዝኩትን ከእጄ ተማረኩ እኔ ባረጅ አታረጅም ሽምግልና አንተን አያውቅ ህም ሕይወቴን አንተ ታድሳለህ ሸለቆዬን በውሃ ትሞላለህ ጥንትም ብርቱ ነህ ዛሬም ብርቱ ነህ ነገም ትኖራለህ ጥንትም ብርቱ ነህ ዛሬም ብርቱ ነህ ነገም ትሰራለህ ሽምግልናዬን ጌታዬ ሆይ አድስ የሕይወቴን ጎዳና ወደ ተስፋህ መልስ በእምነቴም በኑሮ እንዲሁ አርጅቻለሁ ዛሬ በአንተ መታደስን እሻለሁ እምነቴ በፊትህ እጅግ ደክሞ ውስጤ ባዶ ሆኗል ወደ አንተ የሚያራምደኝ ብርታቱ ጠፍሮኛል የቀድሞውን ብርቱነቴን ዓይኔ ማየት ናፍቃ ነፍሴ ጎብኘኝ ትልሃለች ፊትህ ተንበርክካ እኔ ባረጅ አታረጅም ሽምግልና አንተን አያውቅ ህም ሕይወቴን አንተ ታድሳለህ ሸለቆዬን በውሃ ትሞላለህ ጥንትም ብርቱ ነህ ዛሬም ብርቱ ነህ ነገም ትኖራለህ ጥንትም ብርቱ ነህ ዛሬም ብርቱ ነህ ነገም ትሰራለህ እምነቴ በፊትህ እጅግ ደክሞ ውስጤ ባዶ ሆኗል ወደ አንተ የሚያራምደኝ ብርታቱ ጠፍሮኛል የቀድሞውን ብርቱነቴን ዓይኔ ማየት ናፍቃ ነፍሴ ጎብኘኝ ትልሃለች ፊትህ ተንበርክካ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection