አዝ፦ የሚያበራ የንጋት ኮከብ የሆነ ከነገድም ከቋንቋ ሰዎችን ያዳነ የሞትና የሲዖልን መውጊያውን ሰብሮ ጠላትን ጠቢባንንም አሳፍሮ ዳግም ሊመጣ አለ በሰማይ ከብሮ የነገስታትን ኩራት ባዶ ያረገ ለምስኪኖች መንገሻ መንገድ ጠረገ የዚህችን አለም ጥበብ ለማሳፈር እኛን ሞኞች መረጠ ዘላለም ይክበር አዝ፦ የሚያበራ የንጋት ኮከብ የሆነ ከነገድም ከቋንቋ ሰዎችን ያዳነ የሞትና የሲዖልን መውጊያውን ሰብሮ ጠላትን ጠቢባንንም አሳፍሮ ዳግም ሊመጣ አለ በሰማይ ከብሮ ደረቱን በወርቅ መታጠቂያ ታጠቀ ጉስቁልናን ከልጆቹ አራቀ አኖቹ እንደ እሳት ነበልባል ናቸው ጨለማን ያስወገደ ክብሩን ታላቅ ነው አዝ፦ የሚያበራ የንጋት ኮከብ የሆነ ከነገድም ከቋንቋ ሰዎችን ያዳነ የሞትና የሲዖልን መውጊያውን ሰብሮ ጠላትን ጠቢባንንም አሳፍሮ ዳግም ሊመጣ አለ በሰማይ ከብሮ ከሰማይ በአመጻው የተወለደ በምድርም በሰዎች ላይ ሞት ያወረደ ኢየሱስ ከላይ ሲገለጥ የእኛ አባባ ጠላት የለም የታለ የት እንደ ገባ አዝ፦ የሚያበራ የንጋት ኮከብ የሆነ ከነገድም ከቋንቋ ሰዎችን ያዳነ የሞትና የሲዖልን መውጊያውን ሰብሮ ጠላትን ጠቢባንንም አሳፍሮ ዳግም ሊመጣ አለ በሰማይ ከብሮ በአራቱም ማዕዘናት ክብሩ እያበራ ውዳችን ይገለጣል ከመላዕክት ጋራ ከእርሱ ጋር ስንሻገር ከአድማስ ወዲያ ተስፋችን ይፈጸማል ኦ ሃሌሉያ አዝ፦ የሚያበራ የንጋት ኮከብ የሆነ ከነገድም ከቋንቋ ሰዎችን ያዳነ የሞትና የሲዖልን መውጊያውን ሰብሮ ጠላትን ጠቢባንንም አሳፍሮ ዳግም ሊመጣ አለ በሰማይ ከብሮ