Song Lyrics

አማራጭ የለም

Edom Leulseged
Ante Genana
አዝ፦ ኢየሱስ እውነት ሕይወት ነው ኢየሱስ አማራጭ የለው በእርሱ መዳን በእርሱ ነው በሉ (2x) ጌታን የማያውቅ በጨለማ ይኖራል በምድርም ሲኖር ተደናብሮ ያልፋል የዓለም ዝብርቅርቅ ጊዜያዊ እኮ ነው የዘለዓለም ሕይወት ያለው በኢየሱስ ብቻ አዝ፦ ኢየሱስ እውነት ሕይወት ነው ኢየሱስ አማራጭ የለው በእርሱ መዳን በእርሱ ነው በሉ (2x) የፈጠረህማ እጅጉን ቢወድህ አንድያ ልጁን በነጻ እንዲሁ ሰጠህ አንድ ልጁን ሰጠህ ምክንያትን አታብዛ ሰበብህን አቁም ይልቅ ልቦናህን ወደ አምላክም መልስ አዝ፦ ኢየሱስ እውነት ሕይወት ነው ኢየሱስ አማራጭ የለው በእርሱ መዳን በእርሱ ነው በሉ (2x) ነገ ዛሬ አትበል ነገ የአንተ አይደለም የመዳኛ ሰዓት ቢኖር አሁኑኑ ነው ሰዓቱ አሁን ነው አምልጠኸው ውጣ ያሰረህ ጠላት ነው ትብታብህ ይፈታል ኢየሱስን ጌታህ ስታደርገው አዝ፦ ኢየሱስ እውነት ሕይወት ነው ኢየሱስ አማራጭ የለው በእርሱ መዳን በእርሱ ነው በሉ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection