Song Lyrics

በአምላኬ

Edom Leulseged
Ante Genana
በአምላኬ ደስ አለኝ በፍቅሩ ረካሁኝ (2x) ሕዝብህን ለማዳን ፈጥነህ ትነሣለህ የተቀባውንም ትታደገዋለህ እኔስ መጠጋቴ አንተኑ ላምን ነው መፎከሪያዬ ነህ የሚነካኝ ማነው (3x) አዝ፦ ማነው ጌታ እንዳንተ ማነው ማነው እንዳንተ የሚወደው ማነው ኧረ እርሱ ማነው (2x) አቤቱ እንዳንተ የሚሆን አቤቱ እንዳንተ የሚደርስ አቤቱ እንዳንተ የሚወድ አቤቱ እንዳንተ የሚራራ (2x) አንተ የሠራኸው ለእኔ ተቆጠረ ይኸ ደግሞ ሳያንስ ስሜ ተቀየረ ልሳቅ እንጂ በደንብ በከሳሼ ላይ መርገም ተሰበረ ኢየሱስን ሳይ መርገም ተሰበረ መድኃኒቱን ሳይ መርገም ተሰበረ ኢየሱስን ሳይ አዝ፦ ማነው ጌታ እንዳንተ ማነው ማነው እንዳንተ የሚወደው ማነው ኧረ እርሱ ማነው (2x) አቤቱ እንዳንተ የሚሆን አቤቱ እንዳንተ የሚደርስ አቤቱ እንዳንተ የሚወድ አቤቱ እንዳንተ የሚራራ (2x) የጠላቴን ራስ አስረግጠኸኛል ድልን እያበዛህ አስደንቀኸኛል ኩራት ኩራት አለኝ የእኔ እንደሆንክ ሳስብ ፍጥረት ሁሉ ይወቅ አምላኬ መሆንህን (3x) ማነው ጌታ እንዳንተ ማነው ማነው እንዳንተ የሚወደው ማነው ኧረ እርሱ ማነው (2x) በአምላኬ ደስ አለኝ በፍቅሩ ረካሁኝ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection