Song Lyrics

በለቅሶ የዘራሁት

Edom Leulseged
Ante Genana
በለቅሶ የዘራሁትን በደስታ አጨድኩት ምርኮዬም ተመልሷል በብዙ በረከት ሚስጢሩ አንድ ነው የማምለጫው መንገድ እግዚአብሔር ድንቅ ነህ ግሩም ነህ ማለት ጌታን ላመስግን ባልሆነው በሆነው በዚያ ሠፈር ብቻ ድልን ተቀዳጀሁ ዛሬ እንደ ትላንት መች አለቅሳለሁ ቁልፉን አስይዘኸኝ የምሥጋናን በትር ጠላቴን ረግጬ አንበረክከዋለሁ በፎከረብኝ ላይ ቆሜ እፎክራለሁ ከሚውጠው ጉድጓድ ከሚያሰጥም ማጥ አውጥቶ አቆመኝ እግሮቼን በዓለት መች ተንሸራተትኩኝ በቃሉ ላይ ቆሜ ድልን ተቀዳጀሁ እንዲያውም በአምላኬ ልግለጥ ልግለጥ ምርጡን የጦር መሳሪያዬን ላንበልብለው ዛሬ ጠላቴም ይሸበር የመንፈስን ሠይፍ አጥብቄ ይዣለሁ ጠላቴን ቆርጬ አጋድመዋለሁ ከደም ከሥጋ ጋር ውጊያን አቁሜያለሁ ነገሩ ገብቶኛል አሁን ነቅቻለሁ ዘመን መጣ መጣ የዜማ ወራት ከሁሉም ይሰብሰብ ይግባ ለአምላክ ከንፈሮቼን ልክፈት አንደበቴም ያውራው ቅኔም ይደርደር ከዝማሬ ጋራ ታማኝነትህን ማዳንህን ልንገር ሌላ ሰው አልሻም እኔው ነኝ ምስክር ቀረ መሸማቀቅ አቀርቅሮ መሄድ ቀንበር ተሰበረ ቀንቅ ብዬ እንድሄድ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection