ፍርዱ ያምላክ እንጂ እንደ ሰው አይደለ ዓይኖቹ አይተውኛል ጆሮቹ ሰምተውኛል አዝ ይህን ጌታ አከብረዋለሁ! ይህን ጌታ አመልከዋለሁ! አነግሰዋለሁ! ይክበር ! (3x) ይንገሥ ! (3x) ጌታ አይቸኩልም ደግሞም አይዘገይም በጊዜው ይመጣል ዕንባዬን ያብሳል ! አዝ ይህን ጌታ አከብረዋለሁ! ይህን ጌታ አመልከዋለሁ! አነግሰዋለሁ! ውሸት ተደጋግሞ ዕውነት መምሰል ቢቻል ዕውነት ግን ዕውነት ነው ጌታ ኢየሱስ ይፍረድ አዝ ይህን ጌታ አከብረዋለሁ! ይህን ጌታ አመልከዋለሁ! አነግሰዋለሁ! ፊት አይቶ አይመዝንም ውጪ አይቶ አይገመግም ጌታዬን አየሁት ልቤን ግን ሲያነብ አዝ ይህን ጌታ አከብረዋለሁ! ይህን ጌታ አመልከዋለሁ! አነግሰዋለሁ!