Song Lyrics

ሃሌ ሃሌሉያ

Edom Leulseged
Ante Genana
አዝ፣ ሃሌ ሃሌሉያ ማለት ነው የሚያረካኝ እኔ ከዚህ በላይ ሌላ ቃል አይበቃኝ (2x) ተመስገን ተመስገን ተመስገን ጌታዬ ወዳጄ ልልህ እወዳለሁ ባለችኝ ቋንቋዬ (አቅሜ) ዓለም ሳይፈጠር ተመስግኖ ኖሯል ዓለምም ተፈጥሮ እስካሁን ተመልኳል ትልቁም ትንሹም ገናና ብሎታል እኔም ደግሞ አሁን ያንኑ ልደጋግም አዝ፣ ሃሌ ሃሌሉያ ማለት ነው የሚያረካኝ እኔ ከዚህ በላይ ሌላ ቃል አይበቃኝ (2x) ፍልስፍና በዝቶ ዕውቀት ተከማችቶ ጥበብ በጥበብ ላይ ሲታይ ተደርቦ ቆም ብዬ አሰብኩት የፈጠረውን ሁሉንም አዋቁ ብልህ መሆኑን አዝ፣ ሃሌ ሃሌሉያ ማለት ነው የሚያረካኝ እኔ ከዚህ በላይ ሌላ ቃል አይበቃኝ (2x) የሊቅ ዕውቀት ቀርቶ የረቀቀውን መቼ ቀላል ሆነ የሰውስ ጥበብ? ሁሉን ለፈጠረ ለዚህ ድንቅ ጌታ ሃሌሉያ እንጂ ምን ሊባል ነው ታዲያ? አዝ፣ ሃሌ ሃሌሉያ ማለት ነው የሚያረካኝ እኔ ከዚህ በላይ ሌላ ቃል አይበቃኝ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection