እግዚአብሔር የታለ ለምን ትለኛለህ ፍጥረታት በዙሪያህ ከበውህ እያየህ ዓይን አጥርቶ ቢያይ ጆሮችህ ቢያቀኑ የእርሱን ህልውና ታይ ነበር በውኑ ውጣ ወደ ሜዳው ሂድ ወደ ሃይቁ የፍጥረትን ሰሪ ቢያሻህ መጠየቁ አቀበቱን ውጣ ቁልቁለቱን ውረድ ሜዳ ለጥ ያለውን ወይ ረዥሙን መንገድ በደረስክበቱ የሰማህ ያየው ሰሪና ተካዩ ሕያው እግዚአብሔር ነው እያት ቢራቢሮ ተፈጥሮ ያስጌጣት ክንፎቹዋ ርግብግብ ውበት የተሰጣት ተመልከት ወፊቱን ጐጆ ስትራ መሰረቱን ጥላ ለፍታ ጥራ ግራ የትም ዞራ ዞራ በአየር በደመና ተመልሳ ቤቷ ሳትስት ጐዳና አዝ፦ እግዚአብሔርን በእጅህ ቢያሻህ ለመዳሰስ የልብህን ጥያቄ ምናልባት ቢመለስ ተመልከት ፍጥረትን የሰራውን በእጁ ወጥተህ ወደ ደጁ ነፋሱም ያፏጫል ዛፉም ይራወጣል ጂረቱም ይፈሳል ምንጩም ያው ይፈልቃል ቀን ለፀሐይ መውጫ ማታው ለጨረቃ ጨለማና ብርሃን በተራ ጥበቃ ወቅት ሲፈራረቅ ዛሬም እንደጥንቱ እግዚአብሔር ያውልህ እየው በፍጥረቱ አዝ፦ እግዚአብሔርን በእጅህ ቢያሻህ ለመዳሰስ የልብህን ጥያቄ ምናልባት ቢመለስ ተመልከት ፍጥረትን የሰራውን በእጁ ወጥተህ ወደ ደጁ ከፀሐይ ባሻገር ብዙ ዘመን ርቀት እልፍ አእላፍ ክዋክብት ያሸበረቀበት ዓሣ ነባሪውም በውቂያኖስ ጥልቀት አናብስቱ በዱር ሲያገሱ በርቀት ገብረ ጉንዳን ሰልፉ ሁከት የሌለበት ውብ ፍጥረት ዙሪያህን አልመጣ እንደድንገት አዝ፦ እግዚአብሔርን በእጅህ ቢያሻህ ለመዳሰስ የልብህን ጥያቄ ምናልባት ቢመለስ ተመልከት ፍጥረትን የሰራውን በእጁ ወጥተህ ወደ ደጁ