የሚመጣ የሚከብር የሚነግስ ኢየሱስ ተቀናቃኝ የለው ወይም ባላጋራ ፊት ለፊት የሚቆም ግጥሚያ ከርሱ ጋራ ( 2x) በአህዛብ ፊት ሊከብር በድንቅ ይገለጣል ብንወድም ባንወድም ኢየሱስ ይነግሳል ( 2x) የሚመጣ የሚከብር የሚነግስ ኢየሱስ ከእንግዲህ ለውርደት ለሞት አይሰጥም አንድ ጊዜ በመስቀል ፈጽሟል ሁሉንም ( 2x) ያኔ እዳ ሊከፍል ዛሬ ዳኛ ሆኖ ይመጣል ጌታችን በክብር ተክኖ ( 2x) የሚመጣ የሚከብር የሚነግስ ኢየሱስ ከዘመናት በፊት ሁሉን ጥለው ያሉ ለርሱ የተገዙ ሞፈር ቀንበር ሳይሉ ( 2x) በታላቅ እልልታ በሆታ በደስታ በአይናቸው ያዩታል ዘላለሙን ጌታ ( 2x) የሚመጣ የሚከብር የሚነግስ ኢየሱስ ከደመናው መሃል ግርማው የሚያስፈራ በመላዕክት ታጅቦ ከአገልጋዮች ጋራ ( 2x) የቅዱሳን አባት ስሙም አማኑኤል ከከዋክብት ደምቆ አሜን ከተፍ ይላል ( 2x)