Song Lyrics

ኢየሩሳሌም

Dereje Kebede
Adagne Eyesus
አዝ፦ ኢየሩሳሌም ቅድስቲት ከተማ የጐዳናሽ ውጥንቅጡ ቢበዛ እንኳ ሳላይሽ አልቀርም በአምላክ ኃይል እርዳታ ( 2x) የናፈቀኝ ዜማ የቅዱስ ዝማሬ ( 2x) አልቀርም ሳልዘምር ከጻድቃን አብሬ ከበጉ ዙፋን ሥር ሳልዞር በደስታ ( 2x) አልቀርም ሳላይሽ አንቺ ቅዱስ ቦታ ማቋረጫው መንገድ ሊጠልፈኝ ቢነሳ ( 2x) ሳላየው አልቀርም የይሁዳን አንበሳ ብቻዬን ብቀርም መንገደኛው ሸሽቶ ( 2x) ሳላየው አልቀርም ኢየሱሴ መጥቶ የመናኝ ተራራን መቧጠጥ ቢያቅተኝ ( 2x) የበረሃው ጉዞ ውኃ ጥም ቢጐዳኝ የሚያረካው ጌታ ሲመጣ ከሰማይ ( 2x) ይረዳኛል በርግጥ ያቺን ቦታ እንዳይ አዝ፦ ኢየሩሳሌም ቅድስቲት ከተማ የጐዳናሽ ውጥንቅጡ ቢበዛ እንኳ ሳላይሽ አልቀርም በአምላክ ኃይል እርዳታ ( 2x) ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም አዲስ ሕይወት በድል ዳግም የምናይሽ የምንወርስሽ መቼ ይሆን አይቀር ቁርጥ ነው (፫x) ማረፊያችን እፎይታችን ስንወርስሽ ነው ( 2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection