Song Lyrics

አዳኜ ኢየሱስ

Dereje Kebede
Adagne Eyesus
አዝ፦ አዳኜ ኢየሱስ ገናናው የእጄን ሰንሰለት በጠሰው ተመስገን ልበል ለቀኝለት እግሩ ሥር ልውደቅ ልስገድለት ይህም አነሰበት ነፍሴን አስጨንቛት የጥላቴ ጩኸት አይኖቼን ባነሳ ከላይ ስመለከት ከመቅደሱ ሆኖ እምባዬን አበሰ ያሰረኝ ገመድ ጌታ በጣጠሰ አዝ፦ አዳኜ ኢየሱስ ገናናው የእጄን ሰንሰለት በጠሰው ተመስገን ልበል ለቀኝለት እግሩ ሥር ልውደቅ ልስገድለት ይህም አነሰበት የሞትቀንበር ከቦኝ ያመፅ ፈሳሽ ዉጦኝ ሲኦል አፉን ከፍቶ ባጥንቴ አስቀርቶኝ ስሞታ ነገርኩኝ ላምላኬ ሳልሰለች እግዚአብሔር ተቆጣ ምድር ተናወጠች አዝ፦ አዳኜ ኢየሱስ ገናናው የእጄን ሰንሰለት በጠሰው ተመስገን ልበል ለቀኝለት እግሩ ሥር ልውደቅ ልስገድለት ይህም አነሰበት ጠላቴን ሰበረ እንዳያንሰራራ ከቁጣው ጢስ ወጣ ከመቅደሱ በራ ጠላቴን ረገጠ እንደመንገድ ጭቃ ነፃነቴን ሰጠኝ መቆዘሜ በቃ አዝ፦ አዳኜ ኢየሱስ ገናናው የእጄን ሰንሰለት በጠሰው ተመስገን ልበል ለቀኝለት እግሩ ሥር ልውደቅ ልስገድለት ይህም አነሰበት ዛሬማ ሰው ሆኜ ቀስት እገትራለሁ በኮረብታ ሆኜ ምሥጋና እሰዋለሁ ፅኑ እግር ለሰጠኝ የማይንሸራተት ለናዝሬቱ ኢየሱስ ምሥጋና ይብዛለት አዝ፦ አዳኜ ኢየሱስ ገናናው የእጄን ሰንሰለት በጠሰው ተመስገን ልበል ለቀኝለት እግሩ ሥር ልውደቅ ልስገድለት ይህም አነሰበት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection