አሃዱ እላለሁ በምስጋና አፌን እክፍታለሁ በምስጋና እርሱ ያሰበልኝ በለጠና የእኔ ከንቱ ሆኖ ቀርቷልና ወጥቼ ወርጄ ብዙ አስቤአለሁ አውጠንጥኛለሁ ልቤ እሰክሚጨነቅ በስጋት ጉዞ ተክለፍልፌአለሁ ኋላ ግን በየሱስ ተሰብስቤያለሁ /፪ ፈቃዱን አውቄ በምስጋና ቃል ስሙን ጠርቼ እውነተኛ ድምፁን ከአንደበቱ ጠርቶኝ ስምቼ እርሱን እጠብቃለሁ ሌላውን ትቼ /፪ በከንቱ ነበረ መደካከሜ ላይ ታች ማለቴ ነገ ዛሬ እንዲሆን በምኞት ሩጫ እጅግ መትጋቴ አሁን ግን ልቀበል ከላይ ካባቴ /፪ እንግዲህ ካገኘሁ አጋዥ ከአርያም ሐሳቤን ጠቅላይ ደቂቃም አታልፍም አይኔን አንስቼ ወደላይ ሳላይ ድል ይላክልኛል ከሩቅ ከሰማይ /፪