Song Lyrics

ወጥመዱ ተሰበረ

Dereje Kebede
Adagne Eyesus
አቤቱ የታለ ጠላታችን በነነ ከዓይናችን ከእጁ ተወሰደ መውጊያው ቀስቱ የታመነበቱ ወጥመዱ ተሰበረ ሆ እኛም አመለጥን ጠላትም ደረቀ እኛም ለመለምን (2x) ጉድጓድ ተቆፍሮ ነበር ለእኛ ፡ ቁልቁል እንድንገባ እግዚአብሔር ግን ፈጥኖ ፊት ቀደመ ዲያቢሎስ ሰጠመ ወጥመዱ ተሰበረ ሆ እኛም አመለጥን ጠላትም ደረቀ እኛም ለመለምን (2x) በቁጥቋጦ መሃል ጠላት ጠምዶ ሊጥለን አሳዶ ሌት ከቀን አደባ ዐይኑን ከፍቶ መና ሊቀር ለፍቶ ወጥመዱ ተሰበረ ሆ እኛም አመለጥን ጠላትም ደረቀ እኛም ለመለምን (2x) በሰልፍ ያስጨነቀን ብናኝ ሆነ ኃይሉ ተበተነ እንዳረጀ አንበሳ ዝንብ ወረረው ድንፋታው ተለየ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection