ምሕረትህ በእኔ ላይ እንዲሆን እሻለሁ እኔ ግን በቀልን ወዳጅ አድርጌያለሁ ነፍሴ ተጐሳቁላ ከቶም ሳያምርባት ተኮንና እንዳትኖር ይቅርታን አስተምራት ይቅርታን ለማድረግ ልቤ እምቢ እያለው እግሬ የሚራመደው ሸካራ መንገድ ነው የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ ድካሜን ታውቃለህ ዳብሰኝ እንደገና ትለውጠኛለህ ወንድሜን ማቁሰሌ እጅግ ይረሣኛል የተበደልኩትን መቁጠር ይጥመኛል ምናለበት ዛሬ ልቤን ብትጠርበው? መቀጥቀጫው ብረት መዶሻ በእጅህ ነው ይቅርታን ለማድረግ ልቤ እምቢ እያለው(አልሆን እያለው) እግሬ የሚራመደው ሸካራ መንገድ ነው የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ ድካሜን ታውቃለህ ዳብሰኝ እንደገና ትለውጠኛለህ እጄን ለአንተ ሰጠሁ አንተ እንድታስተምረኝ ለውጠኝ ጌታ ሆይ! ይኸው በእግርህ ሥር ነኝ የበደለኝን ሰው ይቅር ብዬ እንዳልፈው በቀልን ሳላስብ በፍቅር እንዳቅፈው ይቅርታን ለማድረግ ልቤ እምቢ እያለው(አልሆን እያለው) እግሬ የሚራመደው ሸካራ መንገድ ነው የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ ድካሜን ታውቃለህ ዳብሰኝ እንደገና ትለውጠኛለህ ምሕረትህ በእኔ ላይ እንዲሆን እሻለሁ እኔ ግን በቀልን ወዳጅ አድርጌያለሁ ነፍሴ ተጐሳቁላ ከቶም ሳያምርባት ተኮንና እንዳትኖር ይቅርታን አስተምራት ይቅርታን ለማድረግ ልቤ እምቢ እያለው(አልሆን እያለው) እግሬ የሚራመደው ሸካራ መንገድ ነው የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ ድካሜን ታውቃለህ ዳብሰኝ እንደገና ትለውጠኛለህ ወንድሜን ማቁሰሌ እጅግ ይረሳኛል የተበደልኩትን መቁጠር ይጥመኛል ምናለበት ዛሬ ልቤን ብትጠርበው? መቀጥቀጫው ብረት መዶሻ በእጅህ ነው