Song Lyrics

ታማኝ ሰው ጠፋ

Dereje Kebede
Yeadinakot Ken Legziabher
ታማኝ ሰው ጠፋ በአገሩ ታማኝ ሰው ጠፋ በምድሩ ሰዎች አላገኙም ቢዞሩ ቢዞሩ በፈረሥም ጠፋ እንኳንስ ሰው በእግሩ ታማኝ ግን በሰማይ አለ በመንበሩ በእርጅናዬ ዘመን አንድ እውነት አገኘሁ አደራ ማይበላ እግዚአብሔር ብቻ ነው ብዙ ወሰደብኝ ሚስጢሩ ሳይገባኝ ይሄ ሰው ማመኔ ደህና አድርጐ ጐዳኝ የዘመናት ጥቅልል የምድር እና ሰማይ የጌታን መመለስ በሁለት ዐይኖቸ ላይ ያወኩት ዛሬ ስአቱ መድረሱን ያበላሁት ወዳጂ ሲያፋጭብኝ ጥርሱን ዘመን ተለዋውጧል (2x) በኩርናን በእንጐቻ ሰው ሁሉ ለውጧል ጨዋነትና ክበር ውህ ፈሰሰበት የቃል አምነት ቀርቷል ፊርማ ከሌለበት ታማኝ ሰው ጠፋ በአገሩ ታማኝ ሰው ጠፋ በምድሩ ሰዎች አላገኙም ቢዞሩ ቢዞሩ በፈረሥም ጠፋ እንኳንስ ሰው በእግሩ ታማኝ ግን በሰማይ አለ በመንበሩ እወየው ጯዋነት ሰፈር ጥሎ ሄዷል ወገን በወገኑ ያልፍርሃት ነግዷል ያስቀመጡት እቃ አይገኝም ዳግም ሁሉ ቃል አጥፊ መሃላ ቢያደርግም ወንድሞቹ ሸጡት ዮሴፍን ለእንጀራ ማዕድ የተጋሩት ሆኑት ባላጋራ የጥንት ታሪክ ነው ዛሬ በዚህ የለም ብዬ ነበር ኋላ በራሴ ሊፈጸም ዘመን ተለዋውጧል (2x) በኩርናን በእንጐቻ ሰው ሁሉ ለውጧል ጨዋነትና ክብር ውህ ፈሰሰበት የቃል እምነት ቀርቷል ፊርማ ከሌለበት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection