Song Lyrics

ምህረት አልወረደም

Dereje Kebede
Yeadinakot Ken Legziabher
እየመሽ ነጋ እየነጋም መሽ ዛሬም ጉስቁልና ከምድሪቱ እልሸሸ የነገዋ ፀሐይ ሙቀት ይዛ ትምጣ የሃገር ልጅ በርዶታል ድሪቶም ስላጣ ከትናንት ዛሬ ይሻል ይሆን ብለን የበጐ ቀን ያለህ አልመጣም ጠብቀን በደረቀ ላንቃ ውኃ እያረረበት አየን በአደባባይ ፍጥረት ሲንከራተት ገና ነው ምህረቱ አልወረደም የሃገሬ ንዳድ ዛሬም አልበረደም ገና ነው ቁጣው መቸ ሰከነ በሽታና ርሃብ በሃደሬ ገነነ በረሃብ ጉስቁልና በጥማት ተቃጥሎ በብርድ ተጠብሶ በፀሐይ ከሳስሎ ኑሮ እንደሬት መሮት ለሞቱ የሚጐመጅ በጐዳናው ከፈፍ ተዘርግቷል እድጅ እየመሽ ነጋ እየነጋም መሽ ዛሬም ጉስቁልና ከምድሪቱ እልሸሸ የነገዋ ፀሐይ ሙቀት ይዛ ትምጣ የሃገር ልጅ በርዶታል ድሪቶም ስላጣ ማረን ጌታችን ፈጽመህ አትቅጣን ጠበልክን እርጨን ጠምቶናል አጠጣን ታማሚው ይፈወስ የራበው ሰው ይጥገብ የፍርድ አዋጅ በቅቶ ምህረቱ ይነበብ ክራራይሶ (2x) እግዚኦ ማሃረነ ክርስቶስ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection