Song Lyrics

የሰው አስታማሚ

Dereje Kebede
Yeadinakot Ken Legziabher
የሰው አስታማሚ ውሱን ነው ስልቹ ይርዳሉ እጆቹ ይከብዳሉ ዓይኖቹ የሰው አስታማሚ ጥቂት ነው ትዕግስቱ ወቅት የማይወስነው ጌታ ማጽናናቱ በራችሁ ተዘግቶ ተረሳን ያላችሁ ውኃ ቀና አድርጐ ጠፍቶ የሚያጠጣችሁ በሩቁም በቅርቡ በያላችሁበት ቁስላችሁ ይጠግግ በጌታ ምህረት አዝ፦ ከአጥር ውዲህ ተከማችተን ጭፍራ ዝላዩን ትተን እስቲ እንውጣ ከአዳራሹ ፍቅር ድጋፍ ወደሚሹ ማነው የሚገደው ለእነኛ አቅም ላጡት ፀሐይ ለማይሞቁ ደጅ ለማይውጡ ከዓይናችን ከጠፉ ፈጥነው ይረሳሉ ኩርሲያቸው ተወስዶ እያሉ እንደሌሉ አዝ፦ ከአጥር ውዲህ ተከማችተን ጭፍራ ዝላዩን ትተን እስቲ እንውጣ ከአዳራሹ ፍቅር ድጋፍ ወደሚሹ ፌጦው ድንገተኛው ሁሉ ተሞክሮ ሃኪሙም ሳይታክት በጥበብ በአይምሮ በሩቅ በጐረቤት ተመክሮ ተዘክሮ እልፍ አልተገኘም ተጥሮ ተግሮ በህክምና ሂደት መድኃኒት ቅመማ በሳይንስ ጥናት በሊቆች ግምገማ የዕድሜያችሁ መጽሃፍ ተከድኗል ያሉአችሁ ወደ ተዓምር ጌታ ይመልከት ዓይናችሁ አዝ፦ ከአጥር ውዲህ ተከማችተን ጭፍራ ዝላዩን ትተን እስቲ እንውጣ ከአዳራሹ ፍቅር ድጋፍ ወደሚሹ ህመማችሁ ጸንቶ ቀና የማትሉት ፋታ የማይሰጣችሁ ውጋት ቀርጥማቱ ውሉ የጠፋችሁ የቀን የሌሊቱ ጌታ ይዳብሳችሁ ባላችሁበቱ በበሽታ አቅም የለ ሥጋ አጥንትህ የሰለለ በፍራቻ ባሕር ስምጠት ሰውም ከቦህ ብቸኝነት ከሃኪሙ ተስፋ አጥተሃል ጤና አዳሙም ሰልችቶሃል እዛው ባልጋው ባለህበት ፈዋሹ አምላክ ይንካህ ድንገት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection