Song Lyrics

የዛሬ ቤተክርስቲያን

Dereje Kebede
Yeadinakot Ken Legziabher
በቀድሞው ስብስብ በአዲስ ኪዳን ህብረት ምዕመናን አብረው በተከማቹበት ንብረቱን ገንዘቡን ሁሉን እያመጣ ማንም ሳይራቆት እንጀራም ሳያጣ በአንድ ልብ ጌታን እያመሰገኑ ይቆርሱ ነበረ ያኔ ምዕመኑ ህብረት እንድናደርግ ያስተማረን ቃሉ እንዲህ ዓይነት ነበር ምዕመን አስተውሉ ዛሬ ቤተክርስቲያን እያሉ የሚጠሩት በየጐዳናው ላይ አስጊጠው የሰሩት አናጢ የዋለበት ከመሰረት ከላይ በቁመት በስፋት ባሻገር የሚታይ ለዓይን ጥጋብ እንጂ ሕይወት የሌለበት ያዘነ የራበው ደጅ የሚቆምበት የነፍሳት ጥሪ ስብከቱ ተረስቶ እቁብ መሰብሰቢያ ሰው ጌታ ቤት መጥቶ የአዲስ ኪዳን ህብረት የሃዋሪያቱ በአንድ ልብ ሁሉም የቆረሱበቱ ሁሉም የኢየሱስ ሥም በልብ በአንደበቱ በዚህ ዘመን ይሁን አሜን ይሁን በሉ ያ ነው የእኔ ጸሎት ለቅዱሳን ሁሉ ሰንበት ጠብቆ እንዲያው ለወጉ መሰባሰቡ ደንቡን ማድረጉ ያለክርስቶስ ኦና ነው ቤቱ ጭፈራው አጉል ዝማሬው ከንቱ የዛሬው ቤተክርስቲያን ባለአስር ሺህ አባላት የቁጥር እሽቅድምድም የአባል ቅጽ ሙላት መቶ የነበረው በሺህ እንዲቆጠር ማን ይበልጥ በብዛት ብሎ መፎካከር ህዝቡ ተጠራቅሞ አዳራሽ ይጠባል ሰው ሰውን አያውቀው ይገባል ይወጣል የዛሬው እረኛ አባላት ይቆጠራል ለጋስና ሃብታሙን ለማግኘት ይጥራል የሥም ቤተክርስቲያን ሞልቷል በየጓሮው ገብተው ለሚያዩት ግን ውስጡ ግን ሌላ ነው መሪዎች ተብለው የሚያስተዳድሩ እንደ ጳውሎስ መስራት ሰንፈው ያልተማሩ ሰርተው የማያውቁ ወንበር የሚያሞቁ በላብ የማግኘትን ሚስጥር የማያውቁ በስልጣን በገንዘብ እርስ በርስ ጡጫ እግዚአብሔር በእነርሱ የዓለም ማላገጫ በየእሁዱ ጉባኤው ስጡ ስጡ ሰፍኖ ከሃብታም ከደሃው ብር ተለምኖ ቀድሞ ከተሰሩት አብልጥ የሚያኮራ ባልሚሊዮን ብር አዳራሽ ሊሰራ የእገሌ ቤተክርስቴን እጹብ ድንቅ ስራ የሰው ልጅ የራሱን ስሙን እንዲያስጠራ ባዶ ሆድ የመጡ የራባቸው ሁሉ ለአዳራሹ መስሪያ ስጡ ይባላሉ በሰንበቱ ህብረት ግራ ቀኝ ላየ ሰው አለ በጌታ ቤት ያጣ የሚቆርሰው ሱሪው የተጣፈ መጫሚያው ያለቀ መቆም የተሳነው አቅሙ የደቀቀ ሞልቷል ውስጡ የሚጮህ በጌታ ፊት ወድቆ የእግዚአብሔር ገንዘብ ግን ባንክ ተጨናንቆ ስስታም መሪዎች ያው ሲስገበገቡ የመንግስት ሲሳይ አይቀርም መሆኑ በእግዚአብሔር ቤት በረከት ይብዛ መብል ይሁን ለራበው በዛ የሳጥኑን ቁልፍ የያዛችሁ የጌታን ገንዘብ ጉዋዳ ያሸሻችሁ ሰማይ ጫፍ ደርሶዋል መሰሰታችሁ ለራበው ለጠማው በትኑት አውጡና የእግዚአብሔርን ገንዘብ ማካበት ይቅርና
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection