የቆምኩበት ስፍራ ይህ ግዑዙ መሬት የሰላም ነው የደም ጠብ የበቀለበት የእርምጃዬ ማብቂያ የእግሮቸን አቅጣጫ መርምር ሩጫዬን የሕይወቴን ምርጫ ልቤን ብትከፍተው ጫካኝ ነው ወይ ገራም የእጆቸ መዘርጋት ለሰይፍ ነው ለሰላም ሌሊት በምንጣፌ በጭርታው ሰዓት የማውጠነጥነው የአዕምሮዬ ሙላት ከአንተ ምን ይደበቃል ፍጥረት እርቃኑን ነው ግልጥልጥ ብሏል ድልድል ቢሆን ገደላማ ብራ ቡሆን ወይ ደመናማ እዚህ በቅርብ ወይ እዚያ በሩቅ ደረቅ መሬት ወይ ውኃ ጥልቅ በምድር በታች በአየር በላይ የሚያልፍ የለም ዓይንህ ሳያይ ዓይኖቼ ተከፍተው ወዴት አማተሩ የምላሴ ቅምሻ ጣፋጭ ነው መራሩ ቃሌ የአንደበቴ የሚወረወረው ለጐረቤት ጆሮ በራድ ወይ እሳት ነው ከአንተ ምን የደበቃል ድልድል ቢሆን