ፀሐይ ፈነጠቀች ደረሰ ጠዋቱ ድምጼም ያስተጋባ የገደል ማሚቱ እግዚአብሔርን ልጥራ በውዳሴ አሃዱ ይነጫነጭ ጠላት ያው እንደልማዱ (3x) ተመቻችቶ ነበር እርስቱን አስፍቶ ዝምታዬ ጣፍጦት ሲቧርቅ ሰንብቶ ስለቴ ደርሶልኝ ለእግዚአብሔር ብዘምር ሽብር ተፈጠረ በዲያብሎስ ቅጥር በማለዳ ዜማ እግዚአብሔር ከበረ ክፋት ሸራቢው ግን ዲያብሎስ አፈረ እርሱ እንዳሻው ይሁን የሲኦሉ ሲሳይ እኔ ግን ልዘምር ላለው ዙፋኑ ላይ በክረምት በበጋ በህመም በጤና በክብር በውርደት በድል እንደገና በማግኘት በማጣት በትርፍ በኪሳራ ስንቱን አቋርጠናል ከእግዚአብሔር ጋራ ዙሬያየን የማየው እልልም ባያሰኝ የክብሩን መስዋእት ልነፍግ እኔ ማን ነኝ በዘመነ መልካም ወይ ዘመን ቁዛሜ እወድሰዋለሁ በሰዎች ፊት ቆሜ በቃላቶች ውበት ጤም ባለው ዜማ ተነሱ እንወድስ ድምጻችን ይሰማ የልባችን ክብደት አስጨናቂው ሁሉ እንደ እያሪኮ ግንብ ይናዳል ከውሉ ጆሯችንን ሰርቆ ሹክ የሚለን ጠላት ሰፍሮ ትከሻችን ሲጭንብን መዓት ማርከሻው መዝሙር ነው ለእግዚአብሔር ምሥጋና ጥንትም የኢየሱስ ሥም መች ይበገርና