አዝ፦ ከሰፈር ሰፈር ውጭ ጉዋሮው ሳየቀር ከበራፍ በራፍ ከቶ አንድም ቤት ሳታልፍ አጽናኝ መንፈስ ሆይ ፈጥነህ ድረስ ለእኛ የምንወዳቸው ተለይተው ከእኛ እስከመቼ ድረስ ሆነን ሃዘንተኛ ሰውማ ዛሬም ላይ ታች ይላል አደባባዩስ መቼ ይጐላል ጨዋ ህዝብ ፈገግታ ያሳያል ልቡ ግን በሃዘን ይጋያል ወንድ ሴት ልጆቹን ያጣ ሰው እህቱን ወንድሙን ያጣ ሰው ወላጆቹን በሞት ያጣ ሰው ያጽናኝ ያለህ ይላል ሆዱን እየባሰው አዝ፦ ከሰፈር ሰፈር ውጭ ጉዋሮው ሳየቀር ከበራፍ በራፍ ከቶ አንድም ቤት ሳታልፍ አጽናኝ መንፈስ ሆይ ፈጥነህ ድረስ ለእኛ የምንወዳቸው ተለይተው ከኛ እስከመቼ ድረስ ሆነን ሃዘንተኛ ባልንጀር አብሮ አደጉን ያጣ የሥራ ባልደራባዉን ያጣ ጐረቤት ጠያቂውን ያጣ የሚያጽናናው ዛሬ ከየት ይምጣ ሞት ያልበዘበዘው ማን አለ ቤት ጓዳው ያልተመሰቃቀለ ተርታውን ከደጃፍ እደጃፍ ነጣቂው ነጠቀ ከቶ አንድም ሳያልፍ አዝ፦ ከሰፈር ሰፈር ውጭ ጉዋሮው ሳየቀር ከበራፍ በራፍ ከቶ አንድም ቤት ሳታልፍ አጽናኝ መንፈስ ሆይ ፈጥነህ ድረስ ለእኛ የምንወዳቸው ተለይተው ከኛ እስከመቼ ድረስ ሆነን ሃዘንተኛ ህጻናት ተጣለ ባዶ ቤት እናት አባት አልቀው በቅጽበት ሽማግሌዎች ጡዋሪም የላቸው ተቀጭተው ተስፋ ልጆቻቸው የፍራቻ ጥላ የሥጋት ሰንብቶአል ምድሪቱን ከዋጣት ጠዋት ያዩት በሕይወት ለማታ በነበር ይወሳል በቅጽበት በአንዳፍታ አዝ፦ ከሰፈር ሰፈር ውጭ ጉዋሮው ሳየቀር ከበራፍ በራፍ ከቶ አንድም ቤት ሳታልፍ አጽናኝ መንፈስ ሆይ ፈጥነህ ድረስ ለእኛ የምንወዳቸው ተለይተው ከኛ እስከመቼ ድረስ ሆነን ሃዘንተኛ ምናልባት ብትራራ ጌታችን የእንጨት ርብራብ ሆኗአል ቤታችን አሳር ነው ዞሮም መግባቱ አባዜው ክፍ ሆኖ የቤቱ ያልፋል ይህ የከፍ ቀን እግዚአብሔር በምረት ሲያውቀን ስብራት ይጠገንና የዓይናችን እንባ ፍፁም ይደርቅና የትናንት ወሬ ይሆንና ይሞላል ሰው በምሥጋና